Page 5 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 5
አብን
የአማራ ሕዝብ ጥቃቶችን የሚመክትለት ተቋም ይቅርና
በመድረክ የሚቆምለት ተቆርቋሪና ወካይ ድርጅት
አልነበረውም፡፡ ይህ በአጋጣሚ ሳይሆን በእቅድና በቅንጅት
የተፈጸመ ታሪክ በማይረሳው የፖለቲካ ሴራ ምክንያት መሆኑ
መታወቅ አለበት፡፡
ትህነግ መራሹ የኢህአዴግ ስርአት የብሄር ፌዴራሊዝምን
ለአስተዳደር መዋቅርና ለስልጣን ምንጭ ሲያውለው የአማራ
ህዝብ ተለይቶ በማንነቱ እንዳይደራጅና ወኪል እንዳይኖረው
በማድረግ ድርብርብ በደል ተፈጽሞበታል፡፡
ሕገመንግስት በማርቀቅና ማጽደቅ ሂደት ውስጥ የአማራ
ህዝብ እንዳይወከል ሲደረግ በህዝቡ ላይ የተለጠፈው
የጨቋኝነት ተረክ የጉባኤው ገዥ ማጠንጠኛ ሀሳብ ሆኖ
አገልግሏል፡፡ የሕገመንግስቱ ሰነድ የአማራን ህዝብ የሚፈርጁ
ሀተታዎችንና አንቀጾችን ከመቅድሙ/መግቢያው/ ጀምሮ
እንዳካተተ ይታወቃል፡፡ ጉዳዩን በተሟላ ሁኔታ ለመረዳት
በሂደቱ ውስጥ የነበሩትን ታሪካዊ የጉባኤ ሀተታዎች
መመልከት ይቻላል፡፡
በሂደት አማራዊ ማንነትን መሰረት ያደረጉ የፖለቲካ
መደራጀቶችን መፍጠር ያስፈልጋል የሚሉ እንቅስቃሴዎች
ላይ ስልጣን ተቆናጥጦ የቆየው ትህነግ መራሹ መንግስትና
ሌሎች አማራ ጠል ጽንፈኛ ድርጅቶች በቅንጅት መጠነሰፊ
ዘመቻዎችን በመክፈት አዳፍነው ለማቆየት ችለዋል፡፡ በሰማዕቱ
ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተመሰረተውን የመላው አማራ
3 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !