Page 61 - DINQ MAGAZINE SEPTEMBER 2020 EDITION
P. 61

ክገጽ 51 የዞረ

                                              ቀማሪው ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው               ምሕረት መሸጋገሪያ ላይ የመጣው መንገድ

       ‹‹በቅዱስ ዮሐንስ ያልዘፈነች ቆንጆ                 ‹‹ኀለፈ ክረምቱ ጸገዩ ጽጌያት ቆመ በረከት!››       ጠራጊው ዮሐንስ ስለሆነ፤ ባህሉ/ ትውፊቱ
       ቆማ ትቀራለች እንደ ሰፈር ጎጆ                    - ክረምቱ አለፈ አበቦችም ፈኩ፣ በረከትም           ከአሮጌው ዓመት ወደአዲሱ መሸጋገሪያዋን
       እቴ አደይ አበባ ነሽ                          ቆመ ይለናል፡፡                            ዕለት፣ መስከረም 1 ቀንን በዘይቤ ‹‹ቅዱስ
       ውብ ነሽ ውብ ነሽ››                                                               ዮሐንስ›› (ዕለተ ዮሐንስ) እያለ ይጠራዋል፡፡
       ዜማውን የሰሙ ጎረምሶች ልጃገረዶቹን እያዩ             የማክሰኞው መስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም.          ከጥንት እስከ ዛሬ ባገልግሎት ላይ
       አፀፋውን ይመልሳሉ፡፡                          በክረምት ውስጥ ይገኛል፡፡  እንደ ቅዱስ ያሬድ  ይገኛል፡፡  ምስጢሩን ባለመረዳት ሚዲያዎች
       ‹‹እንግጫችን ደነፋ                           አመዳደብ፣ በውስጡም ልዩ ልዩ ንኡሳን              በተለይም መንግሥታዊዎቹ በመናገሻ
       ጋሻውን ደፋ                                ክፍሎች አሉት፡፡ ከነሱም መካከል የነሐሴ            ከተማይቱንም ሆነ በየክልሉ የሚገኙት ‹‹ቅዱስ
       እንግጫዬ ነሽ ወይ                            መጨረሻና የጳጉሜን ሳምንት ‹‹ጎሕ፣ ጽባሕ››-  ዮሐንስ›› የሚለውን የመስከረም 1 ቀን ልዩ
       እሰይ እሰይ                                ወጋገን፣ ንጋት ይለዋል፡፡ ይህም ያዲስ ዘመን         መጠርያ ሲያነሱት አይሰማም፡፡ ሃይማኖታዊ
       የቅዱስ ዮሐንስ የመስቀል የመስቀል                  መስከረም የሚጠባበት ጊዜ መድረሱን                ብሎ በመደምደም፡፡
       የላክልኝ ድሪ ሰላላ መላላ                       አመላካች ነው፡፡
       መልሰህ ውሰደው ጉዳይም አይሞላ                                                         በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር አዲሱ ዓመት
                                              ሌላው ንኡስ ክፍል ከዓመት አውራ መነሻ             ዘመን የሚለወጥበት ንጋት 12 ሰዓት ላይ እንጂ
       የዘመን አዋጅ                               (ርእሰ ዐውደ ዓመት) መስከረም 1 ቀን እስከ         እንደ ምዕራባውያን እኩለ ሌሊት (6 ሰዓት)
       መስከረም አንድ ቀን ያለው ልዩ                    መስከረም 7 (8) ቀን ያለው ‹‹ዮሐንስ››          አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ ጋር
       ነገር የዘመኑን መለወጥ አስመልክቶ                  ሲባል፣ ከመስከረም 9 እስከ 15 ዘመነ ፍሬ          የማይተዋወቁት፣ እኩለ ሌሊት ላይ ‹‹አዲስ
       የባሕረ ሐሳብ አዋጁ ይነገራል፡፡                   ይባላል፡፡ ‹‹ዮሐንስ›› የሚለው ቃል              ዓመት ገባ›› እያሉ ማደናገራቸውን ዓመት
       በዓመቱ ውስጥ በዓል                           የተወሰደው በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ                 ዓመት መቀጠላቸውን ሃይ የሚልም ጠፍቷል፡፡
       የሚውልበት፣ ጾም የሚገባባትን                     ከሚገኘውና ኢየሱስ ክርስቶስን ካጠመቀው             ለነገሩ የዘመን መለወጫ እንቁጣጣሽ ዜማዎች
       ቀን መምህራኑ እያሰሉ                          የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ ነው፡፡                  ውስጥ፣ ድምፃውያኑ ቅዱስ ዮሐንስን ፈጽሞ
       ይናገሩታል፡፡ ዓመቱን በፀሐይና                     መስከረም 1 ቀን ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዕለተ            አልረሱትም፡፡ ሁለት የዘመን መለወጫ በዓል
       በጨረቃ፣ በዓመተ ዓለም                         ዮሐንስ መባሉ በተምሳሌታዊ ፍች የመጣ              የሚከበርባት ኤርትራ መስከረም 1 ቀንን
       ለምዕመናኑ ይገልጹታል፡፡ መምህር ዓለሙ               ነው፡፡ ከአሮጌው ብሉይ ኪዳን ወደ ሐዲስ            ‹‹ቅዱስ ዮሐንስ›› እያለች እያከበረችው
       ኃይሌ በምሳሌነት በላሊበላ ያለውን ሥርዓት                             ኪዳን፣ ወደ ዓመተ          መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
       ሲገልጹ የአሥሩም ቤተ መቅደስ ካህናት ቤተ
       ማርያም ይሰበሰቡና ማህሌቱ ካበቃ በኋላ
       ካህኑ ሻሹን ጠምጥሞ፣ ካባ ደርቦ መስቀል ይዞ
       ዘመኑን ያውጃል፣ የባሕረ ሐሳቡን ጥንተ ታሪክ
       ይናገራል፡፡
        አዲሱ ዓመት 2011 ዓ.ም. ተጨማሪ
       አዲስነቱ በዓመቱ ማብቂያ ጳጉሜን 6 ማድረጉ
       ነው፡፡ በአራት ዓመቱ የሚመላለሰውና
       ‹‹ዐውደ ጳጉሜን/ዐውደ ወንጌላውያን
       የሚባለው ሦስተኛ ዓመቱን ይይዛል፡፡ 2011
       ለ4 ተካፍሎ 502 ደርሶ ቀሪው 3 መሆኑን
       ልብ ይሏል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ቤተ
       ክርስቲያን ትውፊት ዘመኑ የሉቃስ መሆኑ
       ያመለክታል፡፡ (1 ከቀረ ማቴዎስ፣ 2 ከቀረ
       ማርቆስ፣ እኩል ከሆነ ዮሐንስ
       ይሆናል፡፡  አዲሱ ዓመት የዓለም ፍጥረት
       መነሻ በሆነው በኢትዮጵያ ዓመተ ዓለም
       ሲቆጠር 7511 ዓመተ ዓለም መሆኑና
       ስምንተኛው ሺሕ ከገባ 510 ዓመታት
       አልፈው 511ኛ ዓመት ላይ መገኘቱን ስሌቱ
       ያሳያል፡፡

       የመስከረም ወቅት
       መስከረም 1 በክረምት ውስጥ የምትገኝ ያመት
       መነሻ ናት፡፡ ሰኔ 26 ቀን የገባው ክረምት
       የሚወጣው መስከረም 25 ቀን ላይ ነው፡፡
       የስድስተኛው መዕት ዓመት የነገረ መለኮት
       ሊቁ (ቲኦሎጊያን)፣ መዝሙረኛውና ዜማ





           DINQ MEGAZINE      September 2020                                           STAY SAFE                                                                                     61
   56   57   58   59   60   61   62   63   64   65   66