Page 100 - Descipleship 101
P. 100

የአክሊል ሽልማት አዲስ ኪዳን ስለ ሶስት ዋና ዋና ፍርዶች ይናገራል፡~
1. የአማኞች ስራ በክርስቶስ ዙፋን ፊት ይፈርድበታል (ይመዘናል)
2. ክርስቶስ በክብር ሲመጣ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ይፈረድባቸዋል (ማቴ. 25፡31-46)
3. በታላቁ ነጭ ዙፋን ፊት የኃጢአተኞች ሙታን ፍርድ (ራዕ.20፡11-15)
የመጀመሪያው ፍርድ ቤተክርስቲያን እንደተነጠቀች የሚካሔድ ሲሆን ሁለተኛው የሺህ አመቱ መንግስት ከመጀመሩ በፊት የሚካሄድ ነው። ሶስተኛው ፍርድ የሺህ አመቱ መንግስተ ሲያበቃ ይሆናል። እውነተኛ አማኝ በመጨረሻው ፍርድ ጊዜ አይኖርም ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ ኃጢያቱ ዋጋውን ከፍሎለታልና ነው (ዮሐ.5፡24፣ ሮሜ.8፡1)።
በትምህርት አስር ላይ እንደተመለከትነው ጌታ ኢየሱስ በዙፋኑ ተቀመጦ የክርስቲያኖችን ስራ ይፈርዳል። በጊዜው ላደረገው ነገር ምዕመን በግሉ መልስ ይሰጣል፤ በተሰጠው ስጦታ በጉልበቱና በገንዘቡ ያደረገውን ይመረምራል (1ቆሮ. 3፡10-15)። ማንኛውም
99




























































































   98   99   100   101   102