Page 98 - Descipleship 101
P. 98
46)። በእግዚአብሄር ላይ የተነሱ መንግስታት ከመሪያቸው ከሰይ ጣን ጋር ለዘላለም ቅጣት ይጣላሉ። ከዚያም ክርስቶስ የሺህ አመት መንግስቱን በምድር ይመሰርታል። ኢየሩሳሌምም የአለም ዋና ከተማ ትሆናለች፤ በዚያም ሺህ አመት ይገዛል (ራዕይ. 20፡1- 6፤ኢሳ.2፡1-5፤ ኢሳ.4፡2-6፤ ኢሳ. 11፡1-9፤ ኢሳ.35፡1-10፤ አሞፅ.9፡13-15)። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ሺህ አመቱ መንግስት ይናገራሉ።
“የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደምውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም
ዲያቢሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፤ ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሄር ቃል ራሶቻቸው የተቆረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፤ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግንባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርሰቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሱ። የቀሩት ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሳኤ ነው። በፊተኛው ትንሳኤ ዕድል ያለው ብጹእና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ስልጣን የለውም፤ ዳሩ ግን የእግዚአብሄርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሳሉ። ”
ለቤተክርስቲያን ንጥቀት እንዴት እንዘጋጃለን?
ምንጊዜም ማስታወስ ያለብን ጌታ ኢየሱስ በማንኛይቱም ደቂቃና ሰዓት ሊመጣ እንደሚችል ነው። ይህንንም ለማወቅ የበለጠ ንጹህና ቅዱስ ሕይወት እንድንኖር ያደርገናል።
97