Page 97 - Descipleship 101
P. 97
ብንመለከት የጌታ ኢየሱስ የመጀመሪያው አመጣጡ በሁለት በሁለት መንገድ ነበር። በመጀመሪያ በቤተልሔም ሲመጣ የተቀበሉት እረኞች ሰብዓ-ሰገድና ሌሎች ጥቂቶች ሰዎች ነበሩ። ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ንጉስ ሲገባ ግን በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ተመልክተውታል (ማቴ. 21፡1-9)። ጌታ ኢየሱስ በሚስጥራዊ መንገድ ሲመጣ የሞቱ ቅዱሳን ይነሳሉ።
በምድር የሚኖሩ ቅዱሳንም ስጋቸው በቅጽበት አይን ይለወጣል፤ ጌታም በአየር ይቀበላቸዋል። ከዚያም ከእርሱ ጋር ወደ መንግስተ ሰማያት ይወስዳቸዋል (1ተሰ.4፡7)። በመጨረሻም ጌታ ለምድር ህዝብ ሁሉ ሊገለጥ በአየር ላይ ብቻ ሳይሆን ወደ ምድር በመላዕክት ታጅቦ ይመጣል በደብረ ዘይትም ተራራ ላይ እግሮቹ ይረግጣሉ (ዘካ.14፡4)።
“በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምስራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምስራቅና
ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፤ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል የተራራውም እኩሌታ ወደ ሰሜን፤ እኩሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል። ”
አንድ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርት ጋር በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ቁጭ ብለው ሳሉ በደመና ታጅቦ ከመላዕክት ጋር ከቅዱሳኑ ጋር እንደሚመጣ ነግሯቸዋል (ማቴ.24፡30፤ 25፡31፤ 1ተሰ.3፡13)። ይህም ከታላቁ መከራ (the great tribulation) በኋላ ይሆናል። ኃጢዓተኛ መንግስታት እስራኤልን ማሳደዳቸውን ያቆማሉ፤ ምክንያቱም ክርስቶስ መጥቶ ሕዝቡን ስለሚታደግ ነው። ከዚያም
በኋላ ክርስቶስ በአለም መሪዎች ላይ ይፈርዳል (ማቴ. 25፡31-
96