Page 95 - Descipleship 101
P. 95
“እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፤ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሀ ግቡ ተመለሱም።” (ሐዋ. 3፡20)
አንዳንዶች ይህ ተስፋ የበዓለ ኀምሳን የሚመለከት ነው ብለው ያስባሉ፤ ሌሎች ክርስቲያን ሲሞት ጌታ ኢየሱስ ወደርሱ ይመጣል ይላሉ። ነገር ግን ስለ በዓለ-ኃምሳ አለመናገሩን እንዴት እናውቃለን? ይህን ከመናገሩ በፊት በክብሩ ስለሚገለጥበት ቀን ነበር። በተጨማሪ ከበዓለ ኀምሳ በኋላ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ስለ ጌታ መምጣት በተደጋጋሚ ተጽፎአል (1ቆሮ.1፡7)። ጌታ ኢየሱስ ስለመመለሱ ሲናገር ስለሰዎች ሞት እየተናገረ አልነበረም። ሞት ከጌታ መምጣት ጋር የሚቃረን ነገር ነው። ምክንያቱም የተናገረው አይለውጥም፤ ታማኝ ጌታ ነውና!
የአዲስ ኪዳን ብቸኛ የታሪክ መጽሀፍ የሆነውን የሐዋርያት ስራን ብንመለከት ምዕራፍ 1፡9-11 ማን ዳግመኛ እንደሚመጣ እንመለከታለን? ኢየሱስ ክርስቶስ በሄደበት ሁኔታ ዳግመኛ ከሰማይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመልሶ ይመጣል። ቤተ ክርስቲያን ተመልሶ ይመጣል፤ ቤተ ክርስቲያን የምትጠብቀውና ተስፋ የምታደርገውም ይህንኑ ነው (ቲቶ. 2፡13)።
ኢየሱስ ለምን ይመጣል?
1. የተናገረው እውነት መሆኑን ለመግለጥ፤
94