Page 96 - Descipleship 101
P. 96
በካህናት ጉባኤ ሊቀ ካህኑ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነና በአብ ቀኝ ሲቀመጥ በደመናም እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር (ማቴ.26፡64)። ይህንን ብዙ ጊዜ ደጋግሞ ስለተናገረ የተናገረውን ለመፈጸም ተመልሶ ይመጣል።
2. አማኞችን ወደ መንግስተ ሰማያት ለመውሰድ፤
የብሉይንም የአዲስንም ኪዳን ጻድቃ ሊወስድ ይመጣል። ስለጌታችን መመለስ የሚናሩትን እነዚህን ጥቅሶች አንብብ፦
• 1ቆሮ.15፡51-58፤ ------------------------------------
• ፊሊጶ.3፡20-21፤ ------------------------------------
• 1ተሰ.4፡13-18) ------------------------------------
ይህ የቅዱሳን በድንገት ወደ ጌታ መወሰድ በመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ መነጠቅ ይባላል፤ ይህም በምስጢር በድንገት ይሆናል። ጌታ ኢየሱስ የራሱ የሆኑትን ልጆች ብቻ መርጦ ከመከራው ዘመን በፊት ከክፉ ያስመልጣቸዋል። የእርሱ ያልሆኑት ግን በዚህ ምድር ላይ ይተዋሉ። የእርሱ ያልሆኑት በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የማያምኑት ናቸው፤ በዚያ ዘመን በብዙ መከራም ይዋጣሉ!
3. ምድርን ለመግዛት፤
ዳግም ምጽዓት ሁለት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው በሚስጥር ወይንም በስውር (private) በርሱ ያመኑት ለመሰብሰብ ሲመጣ ሲሆን፤ ሁለተኛው ግን በግልጥ (in public) በምድር ላይ ለሺህ አመት ለመግዛት ሲመጣ ይሆናል። ወደ ታሪክ ዘወር ብለንም 95