Page 94 - Descipleship 101
P. 94

የክርስቶስ ዳግም ምጽአት
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት በ260 የአዲሰ ኪዳን ምዕራፎች ውስጥ 318 ጊዜያት ተጽፎአል ወይንም በየ25 ቁጥሮች ውስጥ አንድ ጊዜ ተጽፎአል ማለት ነው። ስለ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ለመጀመሪያ ጊዜ መስበክ የጀመረው ሔኖክ ነበር። እርሱም ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ ነበር (ዘፍ.5፡21፤ ይሁዳ፡14-15)። የጌታም የኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻ ንግግሩ ስለዳግም ምዕዓቱ ነበር (ራዕይ. 22፡20)።
“ይህን የሚመሰክር አዎን በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን ጌታ ኢየሱስሆይና።”
ሃያ ሰባቱም የአዲስ ኪዳን መጻህፍት የእርሱን መመለስ ይናገራሉ። በዚህም የጌታ ምጽዓት ምን ያህል ዋና ሃሳብ እንደሆነ እንመለከታለን። አዲስ ኪዳን በአራት ይከፈላል ወንጌላት የሐዋርያት ስራ የጳውሎስ መልዕክቶችና የዮሐንስ ራዕይ ናቸው። ከአራቱም ክፍሎች ጥቅሶችን በመውሰድ ስለ ጌታችን መመለስ እንመልከት።
ክርስቶስ እንደሚመለስ የተስፋ ቃል ለአማኞች ገብቷል
ጌታችን ለደቀመዛሙርት ስፍራ ሊያዘጋጅ እንደሚሄድና ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው ተስፋ ገብቶላቸዋል (ዮሐ.14፡2-3)። ይህንንም የማጽናናት ንግግር የተናገረው ከመሞቱ በፊት
ደቀመዛሙርቱ በሃዘን ላይ ሳሉ ነበር።
93



























































































   92   93   94   95   96