Page 101 - Descipleship 101
P. 101
ነገር አማኝ ሕይወቱን እግዚአብሄር ወይንም ራሱ ይጠቀምበታል። የሰራነውንም ማናቸውም ነገር ጌታ ይፈትነዋል። እሳት እንጨትንና ሳርን ሲያጠፋ ወርቅንና ብርን የከበረን ድንጋይ ግን አያቃጥልም። እንዲሁም ጌታ ለክብሩ ያልተሰራውን ማናቸውንም ነገር ይደመስሰዋል። ብዙዎች ጌታን በታማኝነት በንጹህ ልብ ያገልግላሉ። ስራቸውም ይጸናል። ሌሎች ግን ስራቸው ሲቃጠል ሕይወታቸውን በከንቱ እንዳሳለፉ ይረዳሉ። ነፍሳቸው ግን በጭንቅ ትድናለች።
ጌታ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን እርሱን ለማክበር ብሎ የሰራውን ስራ ያከብራል። ሌሎች ደግሞ ሕይወታቸውን በከንቱ የኖሩ እንጂ ለክርስቶስ ያልኖሩ ያን ጊዜ ያዝናሉ ያሳለፉት ሕይወት የሮጡት ሩጫ ዋጋ ቢስ መሆኑን አውቀው ይጸጸታሉ። ደህንነታችን በእኛ ስራ ላይ ሳይሆን በክርስቶስ በመስቀል ላይ ባደረገው ስራ ሲሆን ሽልማታችን ግን በታማኝነት በተቀበልነው ነገር ጌታን በንጹህ ልብ ባገለገልነው መጠን ነው። አንድ ሰው እንዲህ የሚል ነገር ተናገረ፤ አባት ልጁን ስራ እንዲሰራ ወደ ሌላ ከተማ ላከው ለመንገዱም ገንዘብ ሰጥቶ ከተማ ሲደርስ ማድረግ ያለበትን በግልጽ ነገረው። ጨምሮም በዚያ ከተማ የሚቆይበት ጊዜ ጥቂት በመሆኑ መስራት ያለበትን ነገር ቶሎ ቶሎ በጥንቃቄ መስራት እንዳለበት ነገረው። ልጁም ከተማ እንደደረሰ ወዲያውኑ አባቱ ያላዘዘውን ስራ መስራት ጀመረ። ትንሽ እንደቆየም በከተማ ውስጥ የድሮ ባልንጀሮችን አገኘና ጨዋታ ጀመረ። አባቱ የነገረውን ረስቶ ቆየ። ድንገትም ማድረግ የነበረበትን አስታወሰ ነገር ግን ከከተማ መልቀቅ የነበረበት ጊዜ ደረሰ። አባቱ የሰጠው መመለሻ 100