Page 16 - Descipleship 101
P. 16

መዳኔን እንዴት አውቃለሁ?
አንዳንድ ሰዎች “ድኛለሁ መዳኔንም አውቃለሁ” ይላሉ። እነዚህ ሰዎች በክርስቶስ በማመን የሀጢያትን ይቅርታና የዘላለም ሕይወት ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በውኑ ገና በዚህ አለም እያለን መዳናችንን ልናውቅ እንችላለንን? እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በርግጥ እንችላለን። ሃዋርያው ዮሀንስ ከሞት ወደ ህይወት መሻገራችንን ማወቅ እንደምንችል እንዲህ ሲል ይነግረናል።
“እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል።”( 1ዮሐ.3፡14)
ይህ የደህንነት ማረጋገጫ ማን ሊኖረው ይችላል?
በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ይህ ዋስትና ሊኖረው ይችላል፤ምክንያቱም በቃሉና በመንፈሱ ዳግመኛ ተወልዶ የእግዚአብሄር ቤተሰብ ስለሆነ ነው (ዮሐ.1፡12-13)።
“ለተቀበሉት ሁሉ ግን፤ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሄር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው፤ እነሱም ከእግዚአብሄር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከስጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።”
ብዙዎች ማዳን በማይችሉ ነገሮች ይታመናሉ፤ ነገር ግን ብዙ ቆይተው ማዳን የማይችሉትን እንደታመኑ ይገባቸዋል። የክርስቶስ
15



























































































   14   15   16   17   18