Page 17 - Descipleship 101
P. 17

ኢየሱስ በጎች ብቻ የዘላለም ህይወት እንዳላቸው አውቀው ደስ ይሰኛሉ (ዮሐ.10፡27-28)።
“በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ህይወትን እሰጣቸዋለሁ፤ለዘላለም አይጠፉም፤ ከእጄም ምንም አይነጥቃቸውም።”
የደህንነት ዋስትናን እንዴት ልናገኘው እንችላለን?
አስቀድመን የደህንነትን ዋስትና ልናገኝባቸው የማንችላቸውን መንገዶች እንመልከት፡
• ስሜታችን ዋስትና አይሰጠንም
ስሜታችን ሊያታልለን ስለሚችል በስሜታችን መዳን አለመዳናችንን ወይንም አለመዳናችንን ልናውቅ አንችልም። አንዳንዴ ሰው በጠና ታሞ ሊሰማው የጤነኝነት ስሜት ሊሰማው ይችላል። የህመም ስሜት ተሰምቶት ጤነኛ ሊሆን ይችላል። በማቴዎስ 25፡1-13 ላይ የተጠቀሱት አምስቱ ቆነጃጂቶች ሙሽራውን ለመቀበል የተዘጋጁ መስሏቸው (ተሰምቷቸው ነበር)፤ ነገር ግን በውጪ ተጥለዋል። በማቴዎስ 7፡22-23 እና በሉቃስ 13፡25-27 ላይ የተጠቀሱትም ታሪኮች ከቆነጃጂቱ ታሪክ ጋር ተመሳሳይነት አላቸው።
ስለዚህ አንድ ሰው ሳይድን የዳነ ሊመስለው ይችላል። ምናልባትም እንደዚህ አይነቱን ሰው የሚያታልለው ኃይማኖተኛ 16
  



























































































   15   16   17   18   19