Page 18 - Descipleship 101
P. 18

መሆኑ (religion) ይሆናል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ አይነት ተሳስተዋል፤ ወደ ሲዖልም ገብተዋል። ስሜት ለአንድ ሰው የዘላለም ሕይወት ማግኘትና አለማግኘት አይነገረውም፤ ነገር ግን ሰው የዘላለም ሕይወት ማግኘቱን እርግጠኛ ሲሆን የደስታ ስሜት ሊሰማው ይችላል። እንግዲህ ትክክለኛው ቅደም ተከተል ይህ ነው፦
1. ኃጢያተኛነታችንንና እግዚአብሄር ያዘጋጀልንን የድነት መንገድ እናውቃለን።
2. የተዘጋጀልንን የድነት መንገድ አምነን ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አድርገን እንቀበላለን።
3. ዘላለማዊህይወትንስላገኘንደስታይሰማናል። ትክክለኛው ቅደም ተከተል የሚከተለው ምስል ያሳየናል፡~
 ይህ የባቡል ስእል በደህንነት የቃሉን፣ የእምነትንና የስሜቶችን ቦታና ሚና ያሳያል። የእግዚአብሄር ቃል ሁሌም ቀዳሚ መሆን አለበት። እምነታችን በእግዚአብሄር ቃል ላይ መደገፍ አለበት። ስሜቶቻችን ሁሉ ደግሞ ለእምነችን መገዛት አለባቸው።
17





























































































   16   17   18   19   20