Page 20 - Descipleship 101
P. 20

እርሱም ሚስቱም ቢያረጁም እግዚአብሄር ልጅ እንደሚሰጠው አምኖ ነበር። አብርሃምን እንዲህ እርግጠኛ ያደረገው ምንድን ነው? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀጥተኛ ነው፤ እግዚአብሄር የተናገረውን ስላመነ ነው (ሮሜ.4፡20-21)።
“ለእግዚአብሄርም ክብር እየሰጠ፤ የሰጠውንም ተሰፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፤ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሄር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም።”
ኖኅ እርሱና ቤተሰቡን የሚያድን መርከብ ሰራ። የጥፋት ውሃ እንደሚመጣ ምን አሳሰበው? እግዚአብሔር የተናገረውን ስላመነ ብቻ ነው (ዕብ. 11፡7)
“ኖህ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሄርን እየፈራ ቤተቦቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ። በዚህም አለምን ኮነነ፤ በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። ”
ርዓብ ከኢያሱ ዘንድ የመጡት ሰላዮች ተቀበለቻቸውና ተቀበለቻቸውና በተሰቦችዋን እንዳያጠፉ ቃል አስገባቻቸው (ኢያሱ. 2፡12)።
“ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉ ሁለቱን ሰዎች። ወደ ጋለሞታይቱ ቤት ግቡ፤ ከዚያም ሴቲቱንና ያላትን ሁሉ እንደማላችሁላት አውጡ
አላቸው። ሰላዮችም ብላቴናዎች ገብተው ረዓብን፣ አባትዋንና እናትዋን፣ ወንድሞችዋንም፣ ያላትን ሁሉ፣ ቤተዘመድዎችዋንም ሁሉ አወጡ ከእስራኤልም ሰፈር በውጭ አስቀመጧቸው። ከተማይቱንም በእርሰዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሄር ግምጃ ቤት
19



























































































   18   19   20   21   22