Page 19 - Descipleship 101
P. 19
• የቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን ወይንም የኃይማኖት መሪዎችን ትእዛዝ በመቀበል መዳናችንን ማረጋገጥ አንችልም።
እነዚህ የዘላለም ሕይወት እንዳለን ዋስትና ሊሆኑ አይችሉም ወይንም በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን እንደተመደው ሰባኪ ስብከቱን ሲጨርስ እጃችንን ማውጣት ወይም መቆም ለመዳን ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።
የቤተ ክርስቲያን አባልነት ፎርም መሙላታችን መዘመራችንና ቤተ ክርስቲያን ማዘውተራችን መልካም ነገሮች ቢሆኑም፤ መዳናችንን አያመለክቱንም። ሳንድን የዳንን አስመስሎ ሰይጣን ወደ ዘላለም ጥፋት እንዳይወስደን እምነታችን በእግዚአብሄር ቃል መደገፍ ይኖርበታል። አሁን ደግሞ የደህንነት ዋስትናን የምናገኝባቸውን መንገዶች እንነጋገር።
• በእግዚአብሄር ቃል ምስክርነት አስተማማኝ ነው። 1ዮሐ. 5፡9-12 በልጅ በማመን መዳናችንን ይናገራል።
“የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሄር ልጅ ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ። ”
ሁልጊዜ ሰዎች የሚመሰክሩትን ስናምንበት እንቀበለዋለን ስዚህም እግዚአብሄር ልጁን ስናምን የሚሆነውን ነገር ሲነግረን ማመን ይገባናል። መጽሐፍ ቅዱስ በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው ይለናል፤ ይህን እንዴት እናውቃለን? አጭሩ መልስ እግዚአብሄር ብሏልና!! የሚል ነው። አብርሃም ምንም እንኳን
18