Page 21 - Descipleship 101
P. 21

አደረጉት። ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውን መልእክተኞች ስለ ሸሸገች ጋለሞታይቱን ረዓብን፤ የአባትዋንም ቤተሰብ፤ ያላትንም ሁሉ ኢያሱ አዳናቸው እርስዋ በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጣለች።
ሰላዮቹ ምን ሰጧት? ከከተማይቱ ጋር አብራ እንደማትጠፋ የተስፋ ቃልን ሰጧት፤ ርዓብም ቃላቸውን አመነች። እንደቃላቸውም የተናገሩትን ተስፋ ፈጸሙላት (ኢያሱ. 6፡22-25)። የእግዚአብሔር መልአክ የግብጽን በኩር ይመታ ዘንድ በግብጽ ምድር ባለፈ ጊዜ እግዚአብሄር በበር ላይ ደም ያለበትን ቤት እንዲያልፍ ተናግሮ ነበር ፤ በዚህም ደሙ በተቀባበት ቤት ያሉት ሰዎች የሚያስፈራቸው ነገር አልነበረም፤ ምክንያቱም እግዚአብሄር አነርሱን እንደሚያጠፋ ተናግሮ ነበር። ደሙ መሸሸጊያና መጠበቂያቸው ነበር፤ ቃሉም እርግጠኛ አደረጋቸው (ዘጸ. 12፡13)።
“ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብጽን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም። ”
• የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት
በአዲስ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስን ምስክርነት በተለያየ መንገድ እንመለከታለን። የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ለእኛ መንፈስ ቅዱስ የራሱን ምስክርነት ይሰጠናል (ዕብ. 10፡15) ስለ ምን ይመሰክራል? መንፈስ ቅዱስ በመስቀል ላይ ክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ የሰራውን ስራ፤ ስራውም እኛን ለማዳን በቂ መሆኑንና በተከፈለው
20





























































































   19   20   21   22   23