Page 39 - Descipleship 101
P. 39

በብሉይ ኪዳን ዘመን መንፈስ ቅዱስ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ይወርድ ነበር። ነገር ግን አብሮአቸው አይኖርም ነበር (ዮሐ.7፡39)። መንፈስ ቅዱስ በበአለ ሃምሳ ቀን በተለየ ሁኔታ ወደ ምድር መጣ (ሐዋ.2)። አሁን ግን እግዚአብሄር መንፈሱን በልባችን ውስጥ አፈሰሰው።
የሚከተሉትን ጥቅሶች አገናዝብ (1ቆሮ፡6፡19፤ 12፡13፤ 2ቆሮ. 1፡22)
አዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በእውነተኛ አመኞች ውስጥ እንደሚያድር በግልጽ ይናገራል (ሮሜ.8፡9፤ ኤፌ.1፡13፤ 1ዮሐ. 2፡18- 20)። መንፈስ ቅዱስ በሁሉም እውነተኛ ደህንነትን ባገኙ ክርስቲያኖች ውሥጥ ይኖራል። ነገር ግን ሁሉም አማኞች በመንፈስ ቅዱስ የታተሙ ናቸው እንጂ አልተሞሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ ያዘናል (ኤፌ.5፡18)።
ይህን ትዕዛዝ እንዴት መታዘዝ እንችላለን? በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት ራሳችንን በእግዚአብሄር ፊት በመመርመር፤ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆንና የህይወታችንን ዋና ክፍል ለጌታ መስጠት ያስፈልጋል።
• የመንፈስ ቅዱስ ኃይል
ከሞትና ከኀጢያት ህግ ነጻ ለመውጣት የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያስፈልገናል (ሮሜ.8፡2)። ያለ ፍርኃት እንድንመሰክር መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳን ያስፈልገናል። ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ ለመውጣት የመንፈስ ቅዱስ ኀይል ያስፈልገናል (ሮሜ.8፡2)።
38




























































































   37   38   39   40   41