Page 47 - Descipleship 101
P. 47
ጥምቀትና የጌታ ራት
እግዚአብሄር ለአይሁድ ብዙ የኃይማኖት ስርዓቶችን ሲሰጥ ለክርስቲያኖች ግን ጥምቀትና የጌታን እራት ሰጥቷል። እነዚህም የቤተ ክርስቲያን ስርዓት ወይንም መታሰቢያዎች (ordinances) ተብለው ይጠራሉ። እነርሱም የጌታ ኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ ስለሚያሳስቡን እጅግ በጣም አስፈላጊ ስርዓቶች ናቸው።
እግዚአብሄር እነዚህን ስርአተ መታሰቢያዎች ሲሰጥ ክርስቲያኖችን አንድ እንዲያደርጉ ሲሆን ሰይጣን ግን በእነዚህ ነገሮች ሳቢያ በክርስቶሰ ቤተክርስቲያን መካከል ልዩነትን እየፈጠረና የራሱን ሃሳብ እየመሰረተ ነው (1ቆሮ. 10፡17)። ጥምቀትም ሆነ የጌታ ራት የክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ስለሚያሳስቡን እጅግ በጣም አስፈላጊ ስርዓቶች ናቸው።
የጥምቀት ትርጉም
መጽሀፍ ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ እኛም ከእርሱ ጋር አብረን እንደሞትን ይናገራል(ሮሜ.6፡6)። ሰው ከቤተሰቡ የሚለይበት አንዱ መንገድ ሞት እንደሆነ እኛም ከክርስቶስ ጋር በሞትን ጊዜ ከአዳም ቤተሰብ እንወጣና የእግዚአብሄር ቤተሰቦች እንሆናለን። ነገር ግን እንዴት ሞትን? የእኛ ፍጹም ተወካይ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ሆነን ሞቱን በሚመስል ሞት ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ስንተባበር 46