Page 48 - Descipleship 101
P. 48
ነው፤ ጥምቀትም የዚህ ምሳሌ ነው (ሮሜ. 6፡1-4፤ ቆላ. 2፡12)። ስለዚህ መጠመቅ የሚችሉ እውነተኛ አመኞች የሆኑ ብቻ ናቸው። ምክንያቱም ከክርስቶስ ጋር የሞቱ ስለሆኑ ነው።
“ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሳ እንዲሁ እኛም በአዲስ ህይወት እንድንመላለስ፤ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤”
ሰዎች እንዴት መጠመቅ አለባቸው?
መጽሐፍ ቅዱስ ሰው በሚጠመቅበት ጊዜ ሰውነቱ ሙሉ በሙሉ በውሃ ውስጥ መጥለቅ አለበት ይላል፤ ለምን? በአዲስ ኪዳን ቋንቋ ማለት በግሪክኛ ጥምቀት ማለት መጥለቅ ማለት ነው። ይህም ውኃው የሚጠመቀውን ሰው ሙሉ በሙሉ መሸፈን እንዳለበት ያሳየናል፤ ጥምቀት እንደ ቀብር ነው። ዳግመኛ እንደማናየው አድረገን የሞተን ሰው እንደምንቀብር የሚጠመቀውም ሰው ሙሉ በሙሉ በውሃ መሸፈን አለበት። አማኝ ወደ ውሃ ውስጥ ለጥምቀት ሲገባ የክርስቶስን ሞት ሲተባበር ከውሃው ሲወጣ ደግሞ ከክርስቶስ ጋር በትንሳኤ ይተባበራል ማለት ነው።
47