Page 50 - Descipleship 101
P. 50

የጌታን ራት ለምን መውሰድ ያስፈልጋል?
 በመጀመሪያ የጌታን እራት የምንወስደው ጌታ እራሱ ስለጋበዘን ነው። ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት ምሽት የተወልን ስርዓት ነው። ይህም እንደ ትእዛዝ (command) ሳይሆን እንደ ግብዣ (request) ነው። ኢየሱስ በዮሐ.14፡23 ላይ እርሱን የሚወዱ ትዕዛዙን እንደምፈጽሙ ተናግሯል። ወደ አባቱ ከተመለሰ በኋላ ደግሞ በጳውሎስ በኩል አማኞችን ያሳሰባቸው ነበር (1ቆሮ.11፡23- 24)። ስለዚህ የጌታን ራት የምንሰውደው ጌታ ስላዘዘንና እርሱም ደስ ለማሰኘት ነው።
የጌታ ራት ማን መውሰድ ይችላል?
የጌታን ራት መውሰድ የሚችለው ኢየሱስ ክርስቶስን የህይወቱ ጌታ አድርጎ የተቀበለ ሰው ብቻ ነው። ከዚህ በፊት እንደተጠቀሰው የጌታን እራት የምንወስደው ጌታን ለማስታወስ ስለሆነ፤ ጌታን የማናውቀው ከሆነ እንዴት ልናስታውሰውና ልናስበው እንችላለን? ይህ ቅዱስ ስርዓት የተሰጠው ለአማኞች ብቻ ነው።
ሌላው ደግሞ አንድ ሰው ስለጌታ ራት ምንነት በትክክል ሳይረዳና ያለምንም እውቀት የጌታን ራት (ስጋውንና ደሙን) ቢወስድ አደጋ ላይ ይወድቃል (1ቆሮ. 11፡29)። በመረዳት የሚደረግ ስርዓት በኀጢያት የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ሆነ የሃሰት ትምህርት አስተማሪዎች የጌታን ራት መውሰድ አይገባቸውም (1ቆሮ.5፤11-13፤ 2ዮሐ. 10፡11)። እውነተኛ አማⶉችም ሃሰተኛ አስተማሪዎች
 49





























































































   48   49   50   51   52