Page 51 - Descipleship 101
P. 51
በሚያስተምሩበት ስፍራ የጌታን ራት አብረው መውሰድ የለባቸውም።
የጌታን ራት እንዴት መውሰድ እንችላለን?
የጌታን እራት ብቻችንን የምናደርገው ስርዓት ሳይሆን በህብረት ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር አብረን የምንወስደው ስርዓት ነው። ቤተ ክርስቲያን ከጊዜ ወደ ጊዜ በጌታ ስም (ማቴ. 18፡20) ይህንን ስርዓት ለማካሄድ ትሰበሰባለች (1ቆሮ.11፡26)። ዳግመኛ የተወለደና የክርስቶስ አካል አባል የሆነ ሰው የጌታን ሞት፤ የስጋውን መቆረስን የደሙን መፍሰስ በጌታ ራት ጊዜ ያስባል (1ቆሮ.12፡12)። በህብረት የምንካፈለው ህብስት (ዳቦ) የክርስቶስ ስጋ ምሳሌ ነው።
በህብስቱ መስቀል ላይ የተገረፈውን፥የቆሰለውንና የደማውን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋ ስናስብ በምንጠጣው ወይን ደግሞ ለእኛ ሲል በመስቀል ላይ የፈሰሰው ውድ ደሙን እናስባለን። በዚህ ቅዱስ ስርዓት ከሞተው ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሕብረት እናደርጋለን። ስለ እኛ ብሎ መገፋቱንና ሞቱን ባሰብን ጊዜ ልባችን በአምልኮ ይሞላል።
50