Page 49 - Descipleship 101
P. 49
በአዲስ ኪዳን የጥምቀት ምሳሌዎች
ፊሊጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የደህንነት ወንጌል ከነገረው በኋላ ጃንደረባው ወዲያው መጠመቅ ፈለገ። አብረውም ወደ ውኃ ወረዱና ፊሊጶስ አጠመቀው (ሐዋ. 8፡38-39)። ፊልጶስ ጃንደረባውን ሙሉ በሙሉ በውሃ ውስጥ ማጥለቅ ባያስፈልገው ኖሮ አብሮ ወደ ውኃ ውስጥ መውረድ ባላስፈለገው ነበር። ስለዚህ ጥምቀት ውኃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመጠመቅ ነው እንጂ በመርጨት አይሆንም። መጥመቁ ዮሀንስም በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን ብዙ ውኃ ስለነበር ሰዎችን ያጠምቅ ነበር (ዮሐ. 3፡23)። በየሰው ራስ ላይ ትንሽ ውኃ ቢረጭ ኖሮ ብዙ ውኃ ያለበት ስፍራ ባላስፈለገ ነበር።
የጌታ ራት
የሚከተሉትን ጥቅሶች በጥንቃቄ ተመልከት። ስለ ጌታ ምን ትማራለህ?
§ ማቴ. 26፡26-30፤ § ማር. 14፡22-26፤ § ሉቃ. 22፡19-20፤ § ሐዋ. 20፡7፤
§ 1ቆሮ. 10፡16-17፤ § 1ቆሮ.11. 23-30
48