Page 53 - Descipleship 101
P. 53
ከአለም መለየት
“ስለዚህም ጌታ። ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም
አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። እኔም እቀበላችኋለሁ፥
ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት
ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።”
2ቆሮ.6፡17
እግዚአብሄር እያንዳንዱ አማኝ ከረከሰ ነገር እራሱን እንዲለይ አዟል፤ ይህን የሚታዘዙ አማኞች ደስተኞች ሆነው ይኖራሉ። ሰይጣን ክርስቲያን ከአለም እንዲለይ ሳይሆን ከእግዚአብሄር እንዲለይ፤ እንዲሁም አማኞች እርስ በርሳቸው እንዲለያዪ በብርቱ ይፈልጋል። ለምሳሌ እግዚአብሄር አማኞች አንድ እንዲሆኑ እንደሚወድ ሁሉ ሰይጣን ደግሞ አማኞች አንድ ሲሆኑ ያላቸውን ጥንካሬ ስለሚያውቅ ለማለያየት ይተጋል። በዘመናችን ሰይጣን ሰዎች በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ የተለያየ ሃሳብና አመለካከት ይዘው እንዲለያዩና እንዲከፋፉ በማድረግ ላይ ይገኛል። አማኞች በዚህ አለም ከሚሰራው ከሰይጣን ክፋት መለየት ብቻ ሳይሆን በኑሮና በአስተሳሰባቸው ሁሉ የተለዩ ሊሆኑ ይገባቸዋል ።
“የእግዚአብሄር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን አለም አትምሰሉ። ” ሮሜ.12፡2
52