Page 54 - Descipleship 101
P. 54
በአንደኛ ዮሐንስ 5፡19 አለም ሁሉ በሰይጣን እንደሚገዛ እናነባለን። አለም ማለት እግዚአብሄር የሌለበት ሰው ቦታ ድሎትና እንቅስቃሴን ያጠቃልላል። ክርስቶስ በተፈረደበት ጊዜ አለም ሁሉ ስቀለው፣ ስቀለው፣ አስወግደው ይሉ ነበር። አለም ክርስቶስን ከሰቀለች በኋላ እንኳን እስካሁን ድረስ ስለኀጢአቷ ንስሃ አልገባችም። በዚህም እግዚአብሄር በአለም ላይ ተቆጥቷል፤ ጌታ ኢየሱስም ዳግመኛ እንደ ዳኛ ሊፈርድ ይመጣል (ሐዋ.17፡31፤ ራዕ.19)። ምንም እንኳን ስጋችን አሁንም በአለም ቢሆንም እግዚአብሄር ግን ከዚህ ጠፊ አለም ለይቶናል (ዮሐ. 17፡18)። እኛ ምንም እንኳን ከአለም ኀጢአት ጋር ባንተባበርም ወደ ዓለም ሄደን ወንጌልን እንድንመሰክር ጌታችን ልኮናል (ዮሐ. 17፡18)። ስለዚህ ከዓለም ስላይደለን በዚህ ዓለም ስንኖር እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛ ልንኖር ይገባናል (1ጴጥ.2፡11)። “....እኔ ከአለም አይደለሁም ከአለም አይደሉምና“
የብሉይ ኪዳን የመለየት ምሳሌዎች
መጽሐፍ ቅዱስ ገና ከመጀመሩ ስለብርሃንና ጨለማ መለየት ይናገራል (ዘፍ. 1፡4፤ ዘሌ. 19፡19፤ ዘዳ.22፡9-11)። እግዚአብሄርም ስለመለየት ሊያስተምራቸው እስራኤላውያንን የሚከተሉትን ሶስት ነገሮች እንዳያደርጉ ተናግሯቸው ነበር፦
1. በአንድ እርሻ ላይ ሁለት አይነት ዘር መዝራት
53