Page 56 - Descipleship 101
P. 56

ክርስቲያኖች ከማያምኑ ጋር በመዝናናት፣ በጋብቻ፣ በጋራ ንግድ ስራና በአምልኮ መተባበር ወይንም አንድ መሆን የለባቸውም። ይህ ማለት አለምን ለቀው ይወጡና ለብቻቸው አንድ ደሴት ላይ ይኑሩ ማለት አይደለም። በየዕለቱ ከማያምኑ ጋር ልንቀራረብ ልንመሰክርላቸው እንችላለን። ነገር ግን ከማያምኑ ጋር በማያመች አካሄድ መጠመድ የለብንም።
ሁለት ምድራዊ ነገሮች አሉ፤ እነርሱም ኃጢያትና ዋጋ የሌላቸው (ከንቱ) ነገሮች ናቸው። ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች አንድ ነገር ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብለው ራሳቸው ይጠይቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስም በቀጥታ አድርግ አታድርግ የማይላቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እንደዚህ ላሉት ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አቋም ላልተጻፈለት ጉዳዮች ታዲያ ማድረግ አለብን? አድርግም አታድርግም ላልተባሉ ጉዳዮች ከማድረጋችን በፊት እነዚህ ነገሮች ነገሩን ለመመርመር ስለሚረዱን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራስህን ጠይቅ፦
1. በእርግጥ ይህ ነገር ለእግዚአብሄር ክብር ነው? (1ቆሮ. 10፡31)
2. ባደርገው እግዚአብሄር ከሰጠው ጠቅላላ መመሪያ ወይንም ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ይቃረናል?
3. ባደርገው ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም?
4. እግዚአብሄር እንዲባርከው ልጠይቅ እችላለሁ?
ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች የምንሰጠው መልስ የነገሩን ትክክለኛ መሆን ወይንም አለመሆን ለማየት እንድንችል ይረዱናል።
55



























































































   54   55   56   57   58