Page 57 - Descipleship 101
P. 57

ከአለም የመለየት ውጤት
 ከአለም የተለዩ ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር ፍቅር፤ ኃይልና በረከት ደስ ይሰኛሉ እንጂ በዚህ አለም ከንቱ ነገር አይደሰቱም። እግዚአብሔር ከአለም ለተለዩ ሰዎች ሶስት ተስፋ ገብቶላቸዋል።
“ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኩስንም አትንኩ፤ ይላል ሁሉን የሚገዛ ጌታ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ።”
1. ሊቀበላቸው ቃል ገብቷል፤ እንደ ኃጢዓተኞች ተቀብሏቸው ነበር (ሉቃ. 15፡2)፤ አሁን ግን እንደ ቅዱሳን ደስ የሚያሰኘውን ህብረት እንዲካፈሉ ይቀበላቸዋል።
2. አባት ሊሆናቸው ቃል ገብቷል፤ ከአለም የተለዩ ክርስቲያኖች እግዚአብሄር አባታቸው መሆኑን ያውቃሉ በእርሱም ደስ ይላቸዋል።
3. የእግዚአብሄርወንዶችናሴቶችልጆችይሆናሉ፤በእርሱጥበቃ ስር ይሆናሉ እንዲያገልግሉትም ይረዳቸዋል።
በብሉይ ኪዳን ከአለም የመለየትን ትዕዛዝ ያልጠበቁ አንዳንድ አማኞች ነበሩ። ከእነዚህም ለናሙና ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፦
• ሎጥ ~ በእግዚአብሄር የሚያምን ጻድቅ ሰው ነበር (2ጴጥ. 2፡7-8)። ሆኖም ግን ከአለም ሰዎች ጋር ይተባበር ነበር፤ ከሰዶም ሰዎች ጋር ባልንጀርነት ነበረው (ዘፍ.19)።
56


























































































   55   56   57   58   59