Page 55 - Descipleship 101
P. 55
2. በበሬና በአህያ በአንድ ቀንበር ማረስን ምክንያቱም አንዱ ከንጹህ እንስሳት አንዱ ደግሞ ከረከሱት ወገን ስለሆነ (ዘሌ. 11፡4-8)
3. ከሁለት ዓይነት ነገር የተሰራ ልብስ መልበስ፤ ለምሳሌ ከሱፍና ከጥጥ የተሰራ ልብስ
ከላይ እንደተዘረዘሩት ነገሮች እግዚአብሄር እንድንቀላቀል የማይፈልጋቸው የተለያዩ ነገሮች እንዳሉ መመልከት እንችላለን። እግዚአብሄር እስራኤላውያንን ከግብጻውያን እንደለየ (ዘጸ. 11፡7)። ከሌሎችም ጎረቤቶቻቸው ጋር እንዳይጋቡ ከልክሏቸው ነበር (ዘዳ.7፡3-4)። እንደዚሁ ክርስቲያኖች ከአለም እንዲለዩ አዞናል። በጋብቻና በማይመች ሁኔታ ከማያምኑ ጋር መጣመር እንደሌለብን አዝዞናል።
መጽሐፍ ቅዱስ ጨምሮ እንደሚያስተምረን ሰዎች ለሁለት ጌቶች መገዛት አይችሉም፤ ይህም እግዚአብሔርንና ገንዘብን ሁለቱንም በአንድ ላይ ማገልገል አይቻልም ማለት ነው (ማቴ. 6፡24)። ሐዋርያው ጳውሎስ ኀጢያትን ከሚለማመዱና ክፉን ከሚያደርጉ ጋር እንዳንተባበር ግን እንድንገስጻቸው ይነግረናል (ኤፌ.5፡11)። ክርስቲያንም እንደዚሁ ከኀጢያት መለየት አለበት (2ጢሞ.2፡19)። አለምን እየወደዱ እግዚአብሄርንም መውደድ የማይቻል ነገር ነው (1ዮሐ. 2፡15)።
54