Page 79 - Descipleship 101
P. 79

አምልኮ
ብሉይ ኪዳን እስራኤል ተዋጊ ህዝብ እንደነበረና (ዘኁ. 1፡3) የሌዊ ነገድ ደግሞ አገልጋይ ነገድ እነደነበር ይነግረናል (ዘኁ. 1፡50)። ከእስራኤላውያን ቤተሰቦች መካከል አንዱ ቤተሰብ ደግሞ ካህን ነበር፤ እነርሱም አሮንና ልጆቹ ናቸው (ዘጸ.28፡1)፤ ዘኁ.3፡3)። ካህናት ከሌሎች የተለዩ ናቸው ምክንያቱም ድንኳናቸውን በተለየ ቦታ ተክለዋል፤ ደግሞም የሚለብሱት ልብስና ምግባቸውም እንደዚሁ የተለየ ነበር።
እግዚአብሄር ባለበት ቅዱስ ስፍራ መገኘት ይችሉ የነበሩት እነዚህ ካህናት ብቻ ነበሩ። ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሄር ይቀርቡ ነበር ስለ እግዚአብሄር ደግሞ ወደ ሕዝቡ ይቀርቡ ነበር። በእግዚአብሄርና በሰው መካከል የሚቆሙ ነበሩ። በመሰዊያው ላይ መስዋዕቱን እንዲያቀርቡና ወደ ተቀደሰውም ወደ እግዚአብሄር ክብር እንዲገቡ የተፈቀደላቸው እነርሱ ብቻ ነበሩ።
የብሉይ ኪዳን ካህናት የአዲስ ኪዳን እውነተኛ ካህናት ምሳሌ ናቸው። በአዲስ ኪዳን ካህናት እነማን ናቸው? እውነተኛ አማኞች ሁሉ ካህናት ናቸው ( ራዕይ.1፡5-6፡5፡10፤ 1ጴጥ.2፡5-9)። የእስራኤል ካህናት ይህንን የክህነት ሹመት ያገኙት መሆን ስለ ፈለጉ ሳይሆን ከአሮን ቤተሰብ ስለተወለዱ ብቻ ነው (ዕዝ.2፡62)። በአዲስ ኪዳንም ማንም ሰው ካህን መሆን ስለፈለገ ወይንም ስነመለኮት (Theology) ስለተማረ ካህን መሆን አይችልም።
78






























































































   77   78   79   80   81