Page 80 - Descipleship 101
P. 80
“ለወደደን ከኃጢያታችንም በደሙ ላጠበን፤ መንግስትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን። ” ራዕ. 1፡5-6
በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ ዳግመኛ ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በስተቀር ማንም ሰው ካህን መሆን አይችልም። በ1ቆሮ.12 እና በኤፌ. 4 ላይ ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ተጠቅሰዋል። ክህነት ግን ከእነዚያ መካከል አልተጠቀሰም፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ አማኝ ካህን ለመሆን ስለተጠራ ነው።
ብዙዎች ካህናት ሳይሆኑ ራሳቸውን ካህን ብለው ይሰይማሉ፤ ካህን መሆን የሚችለው በአሮን ቤተሰብ ውስጥ ያለ ብቻ ነው። የአሮን ቤተሰብ በዚህች ምድር በምድራዊ መቅደስ ውስጥ አገለገሉ። በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ ዳግመኛ በመንፈስ ቅዱስ የተወለደ ሁሉ አሁን የእግዚአብሄር ቤተሰብ አባልና ካህን ነው፤ ታዲያ እግዚአብሄርን እንዴት እናገለግለዋለን (ዮሐ. 4፡24)።
ክርስቲያን እንደ ቅዱስ ካህን መንፈሳዊ መስዋዕትን ለእግዚአብሄር ያቀርባል (1ጴጥ. 2፡5)። እንደ ንጉስ ካህን የእግዚአብሄርን ድንቅ ስራ ደግሞ ለሰዎች ይመሰክራል (1ጴጥ.2፡9)።
“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትነግሩ የተመረጠ ትውልድ የንጉስ ካህናት ቅዱስ ህዝብ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ። ”
ለምሳሌ ጳውሎስና ሲላስ ቅዱሳን ካህናትና (ሐዋ.16፡25) እንደ ንጉስ ካህናት (ሃዋ.16፡31) አገልግለዋል። ዕብ.13፡5 ላይም ስለ
79