Page 81 - Descipleship 101
P. 81
ቅዱሳን ካህናት ስራና በቁ.16 ላይ ደግሞ ስለ ንጉስ ካህናት እንመለከታለን። በዚህም ዘመን እንደ አይሁድ ካህናት የተለየ ልብስ እየለበሱ የተለየ ጥቅምና እንክብካቤ “ከቤተ ክርስቲያን” በክህነት ስም የሚያገኙ አንዳንድ ሰዎች አሉ። እንደነዚህ አይነቶች ካህናት በአዲስ ኪዳን ስፍራና ቦታ የላቸውም። ይህ ማለት ግን ሙሉ ጊዜአቸውን በክህነት እንዲያገልግሉ የተጠሩ አገልጋዮች የሉም ማለት አይደለም። ሁላችንም እግዚአብሄርን ለማምለክ የተከፈተ ነጻ መንገድ አለን። አሮን የክርስቶስ ሊቀ ካህንነትን በምሳሌነት ሲያሳይ ልጆቹ ደግሞ ክርስቶስ በደሙ የዋጃቸውን እውነተኛ አማኞችን ያመለክታሉ።
የአምልኮ ትርጉም
ሰው እግዚአብሄርን የሚያመልከው የክርስቶስን የመስቀል ስራ ባስተዋለና ልቡ በምስጋና በተሞላ ጊዜ ነው። ክርስቲያን አብንና ወልድን የሚያመልከው ውድ በሆነ ዋጋ ከኃጢያት ባርነት ነጻ ስለ ወጣ ሊሆን ይገባዋል፤ አምልኮና የእግዚአብሄርን ቃል ማስተማር ሁለት የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል። አምልኮ ከሰው ወደ እግዚአብሄር የሚወጣ ሲሆን የቃሉ ትምህርት ደግሞ ከእግዚአብሄር ወደ ሰው የሚገለጥ ነው። አማኝ ከአብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተረዳውን ሌሎችን ያስተምራል፤ ሲያመልክ ግን በመንፈስ ቅዱስ በወልድ በኩል ወደ አብ አምልኮውን ያቀርባል።
80