Page 83 - Descipleship 101
P. 83
የአምልኮ ሀይል
እግዚአብሄርን በትክክል ማምለክ የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ብቻ ነው (ፊል.3፡3)፤ መንፈስ ቅዱስም ስለ እግዚአብሄር ታላቅነትና ክብር ሲያሳየን ስለ ራሳችን እንድናስብ ሳይሆን ስለ ክርስቶስ ሲያሳየን ደስ ይለዋል። ምን ጊዜም በየትም ስፍራ ለአምልኮ በቀረብን ጊዜ “መንፈስ ቅዱስ ሆይ እግዚአብሄርን እንዳመልከው እርዳኝ ” ልንለው ይገባናል።
የእግዚአብሄር አገልጋዮች በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ
አማኝ ከእግዚአብሄር ጋር ተቀራርቦ ለመራመድ የእግዚአብሄር ቃል ያስፈልገዋል። ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ስለሆነ አካሉን ይመግባል ይንከባከበውማል (ኤፌ.5፡29)። ይህንንም የሚያደርገው ለአንዳንድ አማኞች የስብከትን የማስተማርንና የመንከባከብን ስጦታ እየሰጠ ነው። አማኞች ሁሉ ካህናት ቢሆኑም ሁሉም ግን መምህራንና ሰባኪያን አይደሉም።
በኤፌ. 4፡11-13 ላይ የተጠቀሱት አምስቱም የቤተ ክርስቲያን ስጦታዎች በዚህ ዘመን ላለነው አማኞች ተሰጥተዋል፤ እነርሱም፡-
• ሃዋርያት ~ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ቤተ ክርስቲያን የሚመሰርቱና በመንፈሳዊ ስልጣን ቀዳሚ የሆኑ ናቸው።
• ነቢያት ~ በትምህርት፣ በስብከትና በመንፈስ ቅዱስ መግለጥ ቤተ ክርስቲያንን የሚያንጹ አገልጋዮች ናቸው።
82