Page 85 - Descipleship 101
P. 85
እግዚአብሔርን ማገልገል
እግዚአብሄር ለእያንዳንዱ አማኝ የሚሰራውን የራሱን ድርሻ ሰጥ ቶታል (ማር. 13፡34)። ብዙ ጊዜ አገልጋዮችና ሰባኪያን ብቻ የሚያገልግሉ ይመስለኛል። ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ሰው አካል የተለያዩ ብልቶች አንድ ላይ እንደሚሰሩባት ይናገራል። ራስ እያንዳንዱን ብልት ይመራል። እያንዳንዱ ብልት ደግሞ ከሌላው ብልት የተለየ ስራ አለው። ከብልቶች መካከል ለአካል የማይጠቅም የለም። ብልቶች እርስ በርሳቸው አይጣሉም ይልቁንም ይረዳዳሉ እንጂ። አንዱ ብልት ለሌላው ድጋፍ ነው። ቀኝ እግር ለግራ እግር ያስፈልገዋል። ጣቶችም እርስ በርሳቸው ይፈላለጋሉ።
የሚከተሉትን ጥቅሶች በጥንቃቄ አንብብ፦
• 1ቆሮ.12፡12-32፤ ----------------------------------------------
• ሮሜ.13፡4-8 -------------------------------------------------
• ኤፌ.1፡19-23) ------------------------------------------------
ከእነዚህ ጥቅሶች አራት ታላላቅ ነገሮችን እንመለከታለን።
1. ክርስቶስ በሰማይ የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው
2. በምድር ያለው የክርስቶስ አካል እያንዳንዱን እውነተኛ አማኝ ያጠቃልላል።
84