Page 86 - Descipleship 101
P. 86

3. ራስ ለአማኞች የተለያየ ስራ ይሰጣል፤ ይህም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚሰራ ነው።
4. እግዚአብሄር ያለ ስራ የሚቀመጥ ብልት እንዲኖር አይፈልግም።
የምታገለግለው ጌታ ማነው?
አዲስ ኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኀኒታችንና ጌታችን እንደሆነ
የመቅጣት ስልጣን አለው። ጌታችንም ስለሆነ ማድረግ ያለብንን ይነግረናል። እንድናደርገውም ይፈልጋል። ብዙዎችም ወደ ሲዖል መሄድ ስለማይፈልጉ ክርስቶስን የሕይወታቸው መድኃኒት አድርገው ይቀበላሉ። ነገር ግን የህይወታቸው ጌታ መሆኑን ገና አልተገነዘቡም። ብዙዎች ጌታ ብለው ይጠሩታል ነገር ግን የሚያዝዛቸውን አያደርጉም እንደዚህ አይነት ሰዎች ግብዞች ሆነዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት ካልተረዳን ልናገለግለው አንችልም። ብናገለግለውም አገልግሎታችን ፍሬ አይኖረውም። ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱን የእግዚአብሄር ባርያ እያለ እየጠራ የጌታን ፈቃድ በምድር ይፈልግ ነበር (ሮሜ.1፡1)። ኢየሱስ ጌታ መሆኑን የሚገልጹትን እነዚህን ጥቅሶች ተመልከት። (ሉቃ.2፡11፤ ሐዋ.2፡36፤ ሮሜ. 10፡9፤ ቆላ. 2፡6፤ 1ጴጥ. 3፡13)
የትኞቹ ጥቅሶች የሚከተሉትን ይናገራሉ?
• ክርስቶስ ጌታ ነው? ------------------------------------- 85



























































































   84   85   86   87   88