Page 88 - Descipleship 101
P. 88
አልፈቀደለትም። ሆኖም ግን ባይፈቅድለትም ስለ መልካም ሃሳቡ ግን ባርኮታል። እግዚአብሄርን ማገልገል መልካም ነው ነገር ግን “ለምን እናገልግለዋለን?” ብለን ራሳችንን እንጠይቅ ምክንያቱም የምናደርገው ማናቸውም ነገር ለእርሱ ክብር ሊሆን ይገባልና ነው (1ቆሮ.10፡31)። ጌታ ብቻ የእያንዳንዳችንን የልብ ሃሳብ ስለሚያውቅ በሌሎች ላይ እንዳንፈርድ ልንጠነቀቅ ይገባናል (1ቆሮ.4፡5)። ነገር ግን ጌታ አገልግሎታችንን ሲመዝን መጀመሪያ የልባችንን ሁኔታ (motive) መመርመሩን አንርሳ።
ጌታችን አገልግሎታችንን ይመዝናል
በሌሎች አገልግሎት ላይ ፍርድን መናገር (መተቸት) የለብንም፤ ጌታ ኢየሱስ ራሱ የእያንዳንዱን ምስጢር ወደ ብርሃን ሲገልጥና
የተሰወረ የልብ ሃሳብ ወደ ብርሃን ሲወጣ በዚያን ማን ምን እንደሆነ ስለሚታይ ለመፍረድ አንፍጠን እያንዳንዱ አማኝ በክርስቶስ ሊፈረድ በዙፋኑ ፊት ይቀርባል።
“መልካምም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፡ እያንዳንዱ በስጋው የተሰራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናል” (2ቆሮ.5፡10)
እያንዳንዱም በዚያን ጊዜ ምስጋናውን ከጌታ ዘንድ ይቀበላል (1ቆሮ.4፡5)። ክርስቶስ ስለ ኃጢያት በመስቀል ላይ ስለሞተ እግዚአብሄር በዚያ አይፈርድብንም፤ ነገር ግን ወደፊት ጌታ ኢየሱስ በአገልግሎታችን ላይ ይፈርዳል ያን ጊዜ ፍርዱ “ይድናል ወይስ
87