Page 87 - Descipleship 101
P. 87

• ኢየሱስ ጌታ ነው? --------------------------------------
• ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው? ---------------------------- የምናገልግልበት ምክንያቶች
ምንጊዜም ለምናደርገው ነገር ሁሉ በቂ ምክንያት ሊኖረን ይገባል፤ የምናገልግልበት ምክንያት ከአገልግሎታችን ይልቅ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው። እግዚአብሄር ልብን ስለሚመለከት የምናገለግለው እርሱን ለማክበር ወይም ከሰዎች ምስጋናን ፈልገን እንደሆነ ያውቃል። ጌታ ኢየሱስ የሚያገለግሉት ከልብ እግዚአብሄርን ለማክበር ፈልገው ሳይሆን የሰዎችን የከበሬታ ወንበርና ሙገሳ ስለነበር ፈሪሳውያን አጥብቆ ይቃወማቸው ነበር። የሚሰሩት ስራ ጥሩ ነው ግን የሚሰሩበት ምክንያት (motive) ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ ነበር።
በማር. 9፡41 ላይ ጌታ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርት (ለክርስቲያኖች) አንድ ብርጭቆ ውሃ ስለጌታ ብሎ የሰጠ ዋጋ በሰማያት እንደሚያገኝ ተናግሯል። አንድ ብርጭቆ ውኃ ቀላል ነገር ቢሆንም ስለኢየሱስ ስም ብሎ ሰው ይህንን የሚያደርገው ለክርስቶስ ካለው ፍቅር የተነሳ ብቻ ነው። በፍቅር ነገሮችን የምናደርግ ከሆነ የምናደርግበት ምክንያት (motive) ጤነኛ ነው፤ የሚያስፈልገውም ይህ ነው። ከፍቅር ውጪ የሆነ አገልግሎት በአምላካችን ፊት ምንም ብድራት አናገኝበትም።
ዳዊት እግዚአብሄርን ይወድድ ስለነበር ልቡ ለእግዚአብሄር ቤትን መስራት ተመኘ (2ዜና.6፡8-9)። እግዚአብሄር ግን እንዲሰራለት 86






























































































   85   86   87   88   89