Page 82 - Descipleship 101
P. 82
የአምልኮ ስፍራ
“እንግዲህ፤ ወንድሞች ሆይ፤ በመረቀልን በአዲስና ሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በስጋው በኩል
እንድንገባ ድፍረት ስላለን፤ በእግዚአብሄርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፤ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤”
የእስራኤል ህዝቦች በምድር ላይ በእጅ በተሰራ ቤት እግዚአብሄርን ያመልኩና መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር። ክርስቲያን ግን እግዚአብሄርን ለማምለክ በቀጥታ ወደ እግዚአብሄር ቀርቦ ማምለክ ስለሚችል የተለየ ስፍራ ፍለጋ መሄድ የለበትም (ዕብ.10፡19-22)።
የብሉይ ኪዳን ካህናት መስዋዕትን እንደሚሰዉ እኛም መስዋእትን መሰዋት እንችላለን፤ ይህም ራሳችንን ለእግዚአብሄር በመስጠት ነው (ሮሜ. 12፡1)። ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሄርን በድምጻችን ከፍ አድርገን ልናመሰግነውና ድሆችንም በመረዳት ልናከብረው እንችላለን።
“እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሄር የምስጋና መስዋእት፤ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈራችንን ፍሬ፡ ለእርሱ እናቅርብለት። ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ እንዲህ ያለው መስዋእት እግዚአብሄርን ደስ ያሰኘዋልና። ” (ዕብ.13፡15-
16)
81