Page 66 - DINQ MAGAZINE OCTOBER 2020 EDITION
P. 66
World
Africa
በኮቪድ 19 ምክንያት መኖሪያ ቤት ያጡት ግለሰብ አቶ ማርቆስ ኮኩትስ እስከ
ህይወታቸው መጨረሻ ድረስ መኖሪያ ቤት አገኙ
ማህበረ ረድኤት የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት እና አቶ ማርቆስን ከጎዳና
ለመታደግ ተባብረው ሲሰሩ የነበሩት ጥምር ኮሚቴ ስራቸውን አጠናቀው ቤቱን
ለአቶ ማርቆስ ገንዘቡን ለሞግዚት አስረከቡ።
ነገሩ እንዲህ ነው ፣ ከ35 ዓመት በላይ አትላንታ ውስጥ የኖሩት አቶ ማርቆስ
በአደረባቸው የአእምሮ መረበሽ የተነሳ እና በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ቤት
የሚያከራያቸው ባለመገኘቱ የተነሳ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን የተመለከቱ
ኢትዮጽያውያን እና ኤርትራውያን ለማህበረ ረድኤት በመንገር እና በአካባቢው
09/30/2020
ያሉትን አበሾች በማስተባበር በጋራ ስራ ከጀመሩ ከሁለት ወር በሁዋላ ስራቸውን Johns Hopkins University Africa CDC Dashboard
አጠናቀዋል። ምንም እንኳን ማህበረ ረድኤት እና አስተባባሪ ኮሚቴው ለግለሰቡ
መኖሪያ ቤት ለመግዛት አስበው ስራቸውን ቢጀምሩም ዉጤቱ እነርሱም ሆኑ Georgia
አትላንታ አካቢው ያሉት አበሾች ያልጠብቁት ሆኖ ሁሉንም ተዐምር
አስብሉአል።
ማህበረ ረድኤት እና ኮሚቴው በከፈቱት የጎፈንድሚ አካዉንት
ከ$54000.00 በላይ ሲሰቡለት ከአንድ ደግ ኢትዪጵያዊ ደግሞ አንድ ራሱን
የቻለ መኖሪያ ቤት አቶ ማርቆስ በህይወት እስካለ ድረስ የሚኖርበት ቤት
ለግሰውታል።
ማህበረ ረድኤት እና አሰባሳቢው ኮሚቴም አቶ ማርከስ የተሰበሰበው ገንዘብ
በተለያዩ ምክንያቶች በቀጥታ ለአቶ ማርከስ መስጠት ስላልቻሉ በአቶ ማርቆስ
እና በአሰባሳቢው ስምምነት በአካባቢው ካሉት የሃይማኖት ተቁዋማት በቅርብ
ያለውን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ገንዘቡን በሞግዚትነት
እንዲያስተዳድሩለት የቤተክርስትያኑ አስተዳደር እና ሰበካ ጉባኤ በጹሁፍ
ጠይቀው ቤተክርስትያኑም ጥያቄውን ተቀብለው አስተናግደዋል።
09/30/2020
Johns Hopkins University
በዚህም መሰረት ማህበረ ረድኤት ለቤተክርስትያኑ ገንዘቡን ሲያስረክብ ለአቶ
ማርቆስ በየወሩ የተወሰነለትን ገንዘብ ብሩ እስኪያልቅ ድረስ
በየወሩ የተወሰነለትን ብር ሊሰጡት ፣በአጋጣሚ አቶ ማርቆስ ከዚህ አለም
በህይወት ቢለይ ቀሪውን ገንዘብ ኢትዮጽያ ላለው መቆደኒያ ለተባለው ድርጅት
እንዲሰጥ በሚል ተስማምተው ስራቸውን አጠናቀዋል።
በዚህ አጋጣሚ ማህበረ ረድኤት ለዚህ በጎ ነገር የተባበሩትን ሁሉ እያመሰገነ
በተለይም የመኖሪያ ቤቱን ለሰጡት፣ መኖሪያ ቤቱን ለአደሱት ግብረ ሃይሎች
እንዲሁም ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን አስተዳደር ከልብ
ያመሰግናል።
ማህበረ ረድኤት ማህበር የአሜሪካን ህግን በተከተለ 501C ደረጃ ያለው ህጋዊ
ድርጅት ነው። በማህበረ ረድኤት በኩል የረዱትን እርዳታ ታክስዎን ሲያሰሩ
ማስቀንስ ይችላሉ። በማንኛውም ጊዜ በድርጅቱ ድረ ገጽ
(https://www.mahbereredeat.org)
በመግባት ይርዱ።
Source: MoH Ethiopia
66 “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ” ድንቅ መጽሔት - ጥቅምት 2013