Page 64 - DINQ MAGAZINE OCTOBER 2020 EDITION
P. 64

በየሴምወርቅ ደበበ



       ሰአሊው ስዕሉን ለማሳመር የቀለም ድሪቶ ያበዛባት ስእል    ትዬ ብርሀን የሚለው የጎረቤታቸው ወጣት ልጅ ድምፅ
       ትመስላለች። በፊቷና በፀጉሯ ላይ የተቀባችው የጭቃ ቅብ    ከገቡበት የሀዘን ሰመመን አነቃቸው። እብዷን ፈልገው
       ወዘናዋን አልጋረደውም። ከየት እንደመጣች ባይታወቅም      ነው? ትላንትና እኮ እርሶንና ልጆችዎን ከተተናኮለች
       በቅርቡ ጥሩ ኑሮ የነበራት ውብ ወጣት ስለመሆኗ         በሁዋላ የአእምሮ ህሙማን ማቆያ ነግረን ለሊቱን
       ያልገረጣው ሰውነቷ ያሳብቃል። ከየት እንደመጣች? ማን     መጥተው ወሰዷት እብድ መተናኮል ከጀመረ ያስፈራል ።
       እንደሆነች? በምን አጋጣሚ ለዚህ እንደበቃች መስካሪ      የሌለባትን ፀባይ ከየት እንዳመጣች እንጃ በማለት ዳግም
       በሌለበት በአንድ ጠዋት በአንድ መንደር በአንድ የግንብ    እዛ ቦታ እንደማያገኝዋት አረዳቸው። ይሁን እስኪ - ማን
       አጥር ግቢ ስር ቁጭ ብላ ተገኘች። በያዘችው ስንጥር      ያውቃል ትድን ይሆናል ፣ ይሻላት ይሆናል በማለት
       መሬቱን ከመቆርቆር እና አልፎ አልፎ ከማጉረምረም        እያጉረመረሙ ወደቤታቸው ተመለሱ። የወ/ሮ ብርሀን
       ባሻገር ቀና ብላ ሰውም ሆነ በአካባቢው ያለውን         ባለቤት አቶ አዳም ሰሞኑን ለስራ ጉዳይ ወደ አሜሪካን
       ማንኛውም ነገር አታስተውልም። የሰፈሩ አዲስ እንግዳ      ሀገር ተጉዟል። ባለቤታቸው ለስራ ብዙ ግዜ የሚወጡበት      የያሬድ እናት ነሽ አይደል? ነይ ነይ ላሳይሽ የት እንዳለ ~
       ሆና ከታየችበት ቀን ጀምሮ ከተቀመጠችበት ቦታ          አጋጣሚ በመኖሩ የብቸኝነት ግዜያቸውን የሚያቀልላቸው       እስኪ አንችም ንገሪው ደራሲ ሆኖ የኔን ታሪክ አልፅፍም
       አለመነቃነቋን የተመለከቱ ምግብና ውሀ እየሰጡ በፍርሀት    ልጅ በጉዲፈቻ አምጥቶ ማሳደጉ መሆኑን ከባለቤታቸው        አለኝ ~ ይኸውልሽ ያሬድ ~ አንተ ያሬድ ንገራት ለምን
       ሊያነጋግሯት ይሞክራሉ። በእርሷ በኩል ለብቻዋ          ጋር የተማመኑበት አንዱ ምክንያት ነበር። በትላንትናው      ታሪኬን እንደማትፅፈው ንገራት - ምን ይዘጋሀል ንገራት...
       ከማጉረምረም ባሻገር ለምትጠየቀው መልስ አትሰጥም።       ስልክ በግዜው መቅረብ ባይችሉም ደግመው
       አንቺ ምድር ባሌን በላሽ ........ አሁን ደግሞ ልጆቼን ?   በመደወላቸው ለባለቤታቸው ገጠመኙን              ንገራት.... ንገራት..... ንገራት.... ያሬድ በተሰላቸ ድምፅ
       መቼ ነው የምትጠግቢው?...ማለትን ታዘወትራለች።        ተርከውላቸዋል። አቶ አዳም የባለቤታቸውን ደግነት         ~ ስንት ግዜ ልንገርሽ....እኔ የለሊቷን ንግስት አልወዳትም
       በዚህ የንግግር ስንኟ ላይ ተመርኩዞ መንደርተኛው የራሱን   ያውቃሉ። አይዞሽ አትደንግጭ ~ በልጆች የተጎዳች ሴት      እኔ የማውቃት ንግስት የቀን የቀኗን ነው። እይው ይሄንን
       መላምት አክሎ ታሪኳን ቀርፆላታል። የሰፈሩ ወጣቶች       ትሆናለች የምትችይውን አድርጊላት በማለት              ሞኝ ~ እኔኮ የለሊት ንግስት ነኝ ~ የለሊት ንግስት አበባ
       ለዚህች ሴት መላ እንፍጠር ~ የአእምሮ ህሙማን         ያበረታቷቸውን አስታውሰው የት እንደወሰዷት             ~ ያቺ ለሊት ለሊት እንደሽቶ የምታውደው ~ ቀን ቀን
                                                                                    አንገቷን የምትደፋው የለሊት ንግስት ~ አበባ ~
       ወዳሉበት ቦታ እንውሰዳት እያሉ ይማከራሉ። አዛውንቱ      አጠያይቀው ደረሱበት በሰንበት ሄደው እንደሚጎበኟትም
       ክረምቱ ሳይገባ ለዚች ምስኪን ጠለላ እድርጉላት እያሉ     ለራሳቸው ቃል ገቡ። የጠሩት የኮንትራት ታክሲ ከግቢው      አታቂያትም? በማለት በሳቅ ፍንድቅድቅ አለች ~ ወሮ
       በሀዘን የደማ ልባቸውን ስሜት ይገልፃሉ። በአጠቃላው      አጥር በር ላይ ቆሞ ክላክስ እያደረገ ይጣራል።          ብርሀን በተራቸው አንድም ቃል ሳይተነፍሱ በአግርሞት
       የአካባቢው ነዋሪዎች በሚችሉት ሁሉ ሊረዷት ይጥራሉ።      ያዘገጃጁትን የምግብ ዘንቢል ሰራተኛቸውን አስይዘው        ይመለከታሉ። ከሳቋ መለስ ብላ ያሬድን መወትወት
       ወ/ሮ ብርሀን ደግሞ አንድ ልማድ አስለምደዋታል።        ወደሚጣራው ታክሲ ገብተው ወደ አእምሮ ህሙማኑ           ቀጠለች ~ በል ድርሰቶችህን አሳያት ~ ደራሲ ነው ~
       እንደማትመልስላቸው ቢያውቁም አንድ ቀን ታወራኝ         ማእከል መጓዝ ጀመሩ ~ ቤተሰብ ታሞቦት ነው? ሲል        መፅሀፎች ፅፏል ~ ተነስ አሳያት እያለች ሹራቡን ይዛ
       ይሆናል በሚል ግምት ጥቂት ደቂቃዎች ቁጭ ብለው         የታክሲው ሹፌር ጠየቀ። ዝምድናስ የለንም እንደው እግር     መጎተት ጀመረች። በያሬድ አይን ላይ ጭንቀት ይነበባል ~
       ያዋሯታል። ወ/ሮ ብርሀን ሀብት ሞልቶ የተረፋቸው        ጥሏት በሬ ላይ መጥታ ወድቃ አንስተው ወደዚህ           ትነግርብኛለች ~ ያስሩኛል ~ ይወስዱብኛል ~ እባክሽ
       በልጅ ግን ያልታደሉ ደግ ሴት ናቸው። በቅርቡ በጉዲፈቻ    የአእምሮ ማእከል አስገቧት ~ ብቻ ለምን የዚህች ልጅ      ተይኝ እያለ መማፀን ጀመረ ~ በፍርሀት ለማንም
       ሁለት መንትያ ልጆችን ማሳደግ ጀምረው ደስተኛ እመቤት     ነገር እንዲህ እንቅልፍ እንደነሳኝ አላውቅም ~ ለሊትም     እንዳትናገር ቃል አስገብቶ ተነስቶ ከማእከሉ የመፅሀፍ
       ሆነዋል። እንደተለመደው ሁሉ ዛሬም በእርሷ ትይዩ        እንቅልፍ ሳጣ እሷኑ ሳወጣና ሳወርድ አድራለሁ። አንድዬ     መደርደሪያ ላይ የራሱን መፅሀፎች ይዞ መጣ ይኸውልሽ
       ባለው ድንጋይ ላይ ቁጢጥ ብለው አተኩረው             ምህረቱን ያውርድላት! እንደው ምን ሆና ለዚህ           ~ እንዳትናገሪ ~ ዝምምም ......ዝም..... ባለእጣ፣
       እየተመለከትዋት ያወራሉ። በድንገት መንትያ ልጆቻቸው      እንደበቃች እንጃ ወጣት እኮ ናት እንድ ፍሬ እንዲህ ቆሽሻ   የዲያስፖራ ቅዠት ፣ የጋን ጠጠር እና መረብ የሚሉ
       ወደ እርሳቸው እየሮጡ እማዬ........እማዬ........   እንኳን ቆንጅናዋ የሚገርም ነው አይ የሰው ልጅ መከራ     ርእሶች ነበራቸው ወ/ሮ ብርሀን አንተው ነህ???? እግዚኦ
       ስልክ....ስልክ... ይፈልግሻል... በማለት እስራቸው    እያሉ ሲያወጉት ባለታክሲው ቀበል አርጎ ምን ይደረጋል~     አንተው ነህ???? እያሉ ለመቆጣጠር የከበዳቸውን እንባ
       ደርሰው እንደቆሙ ልጆቼ ........................   ግዜው ያመጣብን ጣጣ ነው ~ ከተማው ሁሉ በእብድ     ዘረገፉት። ስመጥር ደራሲ ነው ~ ያሬድ እና መሰሎቹ
       ልጆቼ........................           ተሞልቷል~ የሚታየውና የሚሰማው ሁሉ ያሳብዳል           የሀገር ሀብቶች በእብዶች እስር ቤት ታጉረዋል ~ አየሽ
       ልጆቼ.........................በሚል የእንባ ሲቃ ጉሮሮዋ   ሰውም እርስ በእርስ ተጨካከነ..... እያለ የመሰለውን ሁሉ   አይደል ነይ ደግሞ ሌላም አሳይሻለሁ እያለች እጃቸውን
       ታንቆ ዘልላ በመነሳት በመንትዮቹ ላይ ተጠመጥማ.....    ምክንያት ከነመሰለው መፍትሄ እየደረደረ ወደ ማእከሉ       መጎተት ጀመረች........ ወ/ሮ ብርሀን በሚያዩት ሁሉ
                                             ደረሱ። ስሟን እንደማያውቁ እና በመልክ እንደሚለዩዋት
       አነባች...... የልጆቹ                       ተናግረው ህሙማኑ ወዳሉበት ይዘዋቸው ገቡ ~            በመገረም እጃቸውን እየጎተተች ስትወስዳቸው ይከተሏት
       መደንገጥ.............................................. የወ/ሮ                     ጀመር። ነይ ~ነይ አሁን ደግሞ መቃብር ቆፋሪውን
                                             አይናቸውን ለማመን ከበዳቸው እንደዚያ እጥፍጥፍ ብላ       ላሳይሽ ~ ነይ ልጆቼን አሳይሻለሁ ብሎኛል ~ ልጆቼን
       ብርሀን የድረሱልኝ ጩኸት..... ................. የእርሷ
                                             ተቀምጣ በዝምታ የምትውለው ወጣት እዚህ እና እዚያ        የቀበራቸው እሱ ነው እያለች ስትመራቸው ፤ አንድ ወጣት
       ለቅሶ... ....አካባቢውን በቅዠት አተራመሰው ግራ      እየተቅበዘበዘች ፊቷ ያገኘችውን ሁሉ ታወራለች። ገና
       መጋባቱ እና ትንቅንቁ በሰፈሩ ጎረምሶች ገላጋይነት ጋብ    በሶስት ሳምንት ቀና ብላ መሄዷ እና መናገሯ የመዳን       ወደ ወ/ሮ ብርሀን እየተጠጋች ~ ፍቅር ይዞሽ ያውቃል?
       ብሏል። ወ/ሮ ብርሀንም ልጆቻቸውን ይዘው በግቢያቸው      ተስፋ እንዳላት ተሰማቸው። ጠጋ ብለው አናገሯት~ አበባ     ~ እኔን ይዞኝ ያውቃል - ጠዋት ማንም ሰው ከእንቅልፉ
       ተሸሸጉ። ማግስቱን ማልደው ተነስተው ቁርስ ብጤ         እባላለሁ ማነው ስምሽ? ስትል ጠየቀቻቸው - ብርሃን       ሳይነሳ ተነስተሽ ወደ ሰማይ ተመልከቺ - የምትወጅውን
       ብትቀምስ ብለው ይዘውላት ወጡ በቦታው ግን            ብርሃን እባላለሁ ታስታውሽኛለሽ? ~ አዎ አቅሻለሁ        ታያለሽ ~ ለእምዩም ነግሬአት ነበር እሷ ግን ጠዋቱን ትታ
       አልነበረችም ደነገጡ እንባቸው በእይናቸው ሞላ። ድንገት                                           ማታ ማታ ሰማዩ ላይ የምትወደውን ትፈልገዋለች -
                                                                                                  ወደ ገጽ  74 ዞሯል

        64                                                                                  “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ”                                                          ድንቅ   መጽሔት -  ጥቅምት  2013
   59   60   61   62   63   64   65   66   67   68   69