Page 28 - DINQ Magazine June 2020 Edition
P. 28

የወሩ ጉዳይ ከገፅ 13 የዞረ

       ራስን  ከወረርሽኙ  ለመከላከል  የሚጠቅሙ  የሳኒታይዘርና  የማስክ
       እጥረት መከሰቱ  አይዘነጋም፡፡ ለብዙዎች አግራሞትን የፈጠረው ግን
       የመፀዳጃ ቤት ወረቀት እጥረት በከፍተኛ ደረጃ መከሰቱ ነው፡፡ በተለይ
       አሜሪካውያን የኮሮና ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ፣ ከሌሎች ሸቀጦች
       በተለየ  የመፀዳጃ  ቤት  ወረቀት  በብዛት  ነበር  የሚገዙት፡፡  ምክንያቱ
       በትክክል ባይታወቅም፡፡ (በነገራችን ላይ ወረርሽኙ ተባብሶ ምናልባት
       ሥርዓት አልበኝነት ቢፈጠር በሚል፣ የሽጉጥና የጠብመንጃ ሽያጩም
       ደርቶ ነበር)
           ከኮቪድ-19 መከሰት ጋር ተያይዞ የተስተዋለውን የመጸዳጃ ቤት
       ወረቀት ከፍተኛ ፍላጎት የተገነዘበው በአሜሪካ የኦሪገን ፖሊስ መምሪያ፣
       ባለፈው መጋቢት ወር መባቻ ላይ በፌስቡክ ያሰፈረው መልዕክት ፈገግታን
       የሚያጭር ነው፡፡ (ለፖሊስ መምሪያው ጭንቀት የወለደው ቢሆንም)
           በኦሪገን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ፣ ፖሊስ ለነዋሪዎች
       ያስተላለፈው  መልዕክት  እንዲህ  ይላል፡-‹‹የመፀዳጃ  ቤት  ወረቀት
       አለቀብን  ብላችሁ  ብቻ  9-1-1  እንዳትደውሉ፡፡  ችግሩን  ያለ  እኛ
       እርዳታ ልትወጡት ትችላላችሁ፡፡››
             ፖሊስ  ይህን  መሰሉን  መልዕክት  በፌስቡክ  ላይ  ማስፈሩ  ምቾት
       እንዳልሰጠውም ሳይገልጽ አላለፈም፤ግን ሌላ ምርጫ አልነበረኝም ባይ
       ነው፡፡
            በመጨረሻም ‹‹ይህም ያልፋል›› ሲል ለነዋሪዎች የመጽናኛ
       ቃል  ያስተላለፈው  የኦሪገን  ፖሊስ  መምሪያ፤  ‹‹አደራ  የመጸዳጃ
       ቤት ወረቀት አልቆብናል ብላችሁ እንዳትደውሉ፤ እኛ ልናመጣላችሁ
       አንችልም፡፡›› በማለት እቅጯን ተናግሯል፡፡















































             Page 28                                                           “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር“                ድንቅ መጽሔት -  ሰኔ 2012
   23   24   25   26   27   28   29   30   31   32   33