Page 46 - DINQ Magazine June 2020 Edition
P. 46

አንድ ለመንገድ                                                ድልድይና ጎዳናን መስራት የጀመሩት ደሞ ብጤዎቼ ይመስሉኛል
                                                                ፤ ስራ ላይ ራሱ ተመልከቺ ፤ አሁን ወንድ ልጅ ምንም ቢገደድ
                                                                ሁለት ሰአት ሙሉ ብቅል ሊፈጭ ይችላል? ራሱን በወፍጮው ልጅ
                                                                ፈጥፍጦ ቢገል ይቀለዋል፤ ታይፒስት መሆን ይችላል? ወንድ ልጅ
                                                                ባንድ ቦታ ቁጭ ብሎ የሚሰራው ስራ አለ? እንጃ! ምናልባት
                                                                ልብስ ሰፊነት ? እሱንም ቢሆን ታግሶ የተቀበለው ከታች እግሩን
              እህ                                                ማንቀሳቀስ ስለሚችል ነው፤ ልብ ብለን ካየነው የሽመና ስራም
                                                                የቅምጥ  ስራ  አይደለም  ፤ሰውየው  ባይንቀሳቀስ  ቆለጡ  እሱን
            እንዴት ነው            ገዳዎ!                             ወክሎ ወድያ ወዲህ ይላል ፤
                                                                      ምን  ልል  ፈልጌ  ነው?  ቀሳው  በዚህ  ከቀጠለ  ወንዶች
                                                                ከነጨርቃችን  እናብዳለን  ፤ሴቶች  እንደነበሩት  ይቀጥላሉ፤ግፋ
      (በእውቀቱ ሥዩም)                                               ቢል ወንዱ አብዶ ሲፈነዳ ፍንጣሪው ቢነካቸው ነው፤
                                                                      እኔኮ  በራሴ  አየዋለሁ፤  እግሬ  ቢታሰር  አእምሮየ
            በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት የመጀመርያው የሰው ልጆች ስራ                 ይንቀዠቀዣል፤  ሁለት  የዩቲውብ  ሳንዱቅ  ከፍቼ  አንዱን  ሳላይ
      አደንና ፍራፍሬ መልቀም ነበር፤ አንድ ወንድ እና ሴት ተጣምረው ዱር                ወደ  ሌላው  እዘልላለሁ::  ልደቱ  አያሌውን  መስከረም  ሰላሳ
      ለዱር ይንከራተታሉ:: እንጆሪ ለቅመው ወይም የዱር ፍየል አድነው                  ላይ አስደግፌ ወደ ባህሩ ቃኘ የሄድኩበት ፍጥነት ጉግልን ራሱ
      በጋራ ይበላሉ፤ከእለታት አንድ ቀን ሴቲቱ ታረግዛለች፤                         ሳያሳስበው አልቀረም:: what is the attention
            ሆዷ ገፍቶ እንደ ድሮው ዛፍ መውጣት ወይም መስክ በሩጫ                  deficient  hyperactivity  disorder
      ማቋረጥ  በሚሳናት  ጊዜ  ባልየው  አንድ  ዋሻ  ውስጥ  ጥሏት  ወይም             የሚል እርእስ ያለው ሌክቸር ሪኮመንድ አደረገኝ፤
      አስጠልሏት ይሄዳል፤ ገራም ከሆነ ዞሮ ዞሮ ይመለሳል ፤ የተረገመ ከሆነ                    በነገራችን ላይ እያንዳንድሽ እግዜር ባያይሽ ጉግል ያይሻል፤
      እንደወጣ  ይቀራል፤  ቀስ  በቀስ  ሴቷ  ባንድ  ቦታ  ልትረጋ  የተፈጠረች          ባለፈው፤ ባለንጀራየ በየነ ገላውን ታጥቦ፤ መቸም ብቻየን ነኝ
      መሆኑን ትረዳለች፤ ጎጆም ትቀልሳለች::                                  ብሎ፤ ላፕቶፑን ሳይዘጋ ታችኛውን ላጨ:: ከዛ ዩቲውብ ገብቶ
            ባንድ  ቦታ  ረግቶ  መቀመጥ  በሴት  ሆርሞን  ውስጥ  ያለ  ነገር         ባህላዊ ዜማ እየሰማ እያለ Recommended for you
      እንደሆነ  ሁሉ  ፤  መቅበዝበዝ  በወንድ  ልጅ  ደም  ውስጥ  ያለ  ነገር          እሚል መጣለት፤ እና ጎግል የመረጠለትን ቢድዮ ርእስ ሲሾፈው
      ነው:: ሲሄድ ውሎ ሲሄድ የሚያድር ወንድ እንጂ ወንዝ አይደለም፤                  ምን  ይላል፤  How  to  enlarge  your  penis
      ወንድ ልጅ የእመቤቶች ለማዳ እንስሳ ከመሆኑ በፊት ባንዲት ጣራ                   without a medical aid .
      ስር እሺ ብሎ እሚቸከል ፍጡር አልነበረም፤ እንዲያም ሆኖ ፤ሰበብ                        አርፌ ባህሩ ቃኘን ባዳምጥስ ?
      እየፈጠረ፤ወታደር፤(ዋትቶ- አደር) ሲራራ ነጋዴ፤ ፖስታ አመላላሽ                        እህ እንዴት ነው ገዳ-ዎ
      ፤  አሳሽና  ሀዋርያ  አድርጎ  ራሱን  እየሾመ  የመሄድ  ሱሱን  ሲያረካ                 እንዴት ነው ገዳ-ዎ
      ኑሯል::                                                           እንዴ?      ባህሩ  ቃኘ  ስለገዳ  ስርአት  መዝፈናቸውን
            ቤት  መስራትና  መንደር  ምስረታን  የጀመሩት  ሴቶች  ሲሆኑ             እንዴት እስከዛሬ ልብ ሳልል ቆየሁ?














































            Page 46                                                           “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር“                ድንቅ መጽሔት -  ሰኔ 2012
   41   42   43   44   45   46   47   48   49   50   51