Page 49 - DINQ Magazine June 2020 Edition
P. 49

ቅምሻ 2






                                                                                                     *******  *******





        ጠብታ ማር

         --------------------------------------------------------------------------
               ለምሳሌ ልጅህ ሲጋራ እንዳያጨስ ብትፈልግ ስለ ሲጋራ መጥፎነት አትስበክለት፡፡ ሆኖም ሲጋራ ማጨስ የአንድ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች
        እንዳይሆን ወይም በሩጫ ውድድር እንዲሸነፍ የሚያደርገው መሆኑን ንገረው፡፡
               የሌላውን ፍላጎት የመጠበቅ ነገር ከማንኛውም ነገር ጋር ማለትም ከሕጻናት ወይም ከጥጃ ወይም ከዝንጀሮ ጋር በምናደርገው ግንኙነት ሁሉ
        ሊታሰብበት የሚገባ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰንና ልጁ አንድ ቀን አንድ ጥጃ ወደ ጋጥ ለማስገባት ሞከሩ፡፡ ሆኖም አብዛኛው ሰው
        የሚፈፅመውን ስህተት ፈፀሙ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን እንጂ ጥጃው የሚፈልገውን አላደረጉም፡፡ ኤመርሰን ከኋላ ወድሮ እምቢ አለ፡፡ ይህን ከንቱ ጥረቱ ታይ

        የነበረችው ሠራተኛ ጥጃው ምን እንደፈለገ ገባት፡፡ ጠጋ አለችና ጣቷን በዘዴ ለጥጃው አጎረሰችው፡፡ ጥጃው ጣቷን መጥባት ሲጀምር ቀስ ብላ ወደ ጋጡ
        እየተራመደች ይዛው ገባች፡፡ ሠራተኛው ምንም እንኳን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ ባይኖራትም በዚያች ወቅት ከኤመርሰን የበለጠ ማስተዋል ችላ ነበር፡፡
               ከተወለድክ ጀምሮ ያደረግካቸውን ለምሳሌ ለቀይ መስቀል ማኅበር 100 ብር የሰጠህበት ጊዜ ቢኖር እንኳን ሌላውን ከመውደድ የመነጨ በጎ ሥራ

        ለመሥራት ስለፈለግህ ነው፡፡ ከመርዳት ፍላጎትህ ይልቅ የብር ፍላጎትህ ቢያይልብህ መቶ ብሩን ባልሰጠህ ነበር፡፡ እርግጥ አስተዋጽኦው እንድታደርግ የጠየቀህ
        ሰው እምቢ የማትለው ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ እውነት አለ፡፡ ብሩን የሰጠኸው ምናልባት ከሰውየው አንድ የፈለግከው ነገር ስለነበረ ነው፡፡
               ዴል ካርኒጌ፣ “ጠብታ ማር” (1989)
                             በሁለቱ ስዕሎች መካከል 7 ልዩነቶችን ያውጡ Get 7 Differences













































              DINQ    magazine   June   2020   #209                                       PLEASE    BE    SAFE    and    Happy   Father's    Day                                                                            Page 49
   44   45   46   47   48   49   50   51   52   53   54