Page 74 - አብን
P. 74
አብን
የሀይማኖት ጉዳዮች፤ በመብት መገልገልን ጨምሮበተለያዩ
ሀይማኖቶች መካከል ያሉትን መስተጋብሮችና ወሰኖች
ለመዳኘት፤ የወንጀል ህጉን ጨምሮ በሌሎች ህግጋትና
በሀይማኖት ነጻነት መካከል ያሉትን የአድማስ ጥልፍልፎሽ
በህጋዊ ስርአት ለማስተዳደር ስላልተቻለ የተለያዩ የመንግስት
መዋቅሮች በህገወጥ አሰራርና በጣልቃ ገብነት የአድሎ
ተግባራትና የመብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል፡፡ በተለይ
የሀይማኖት ነጻነትን በተመለከተ የተጻፉ ድንጋጌዎች ሰፋ
ተደርገው መተርጎም እንዳለባቸው፤ በግልጽ ህግጋት ቅቡል
በሆነ መልኩ ከተቀመጡ ገደቦችና ክልከላዎች ውጭ በመብቶቹ
መገልገል ፍቅድ እንደሆነና ምንም አይነት ተጨማሪ ክልከላም
ይሁን ገደብ ማድረግ እንደማይቻል እየታወቀ በተለያዩ
የሀገሪቱ አካባቢዎች፤ በህዝብ አስተዳደር ተቋማት፤ በመስሪያ
ቤቶችና በትምህርት ተቋማት አስተዳደሮች ጭምር
ከስልጣናቸው ውጭ በየጊዜው የመሰላቸውን አፋኝና ግጭት
ቀስቃሽ መመሪያዎችን እያወጡ ለመተግበር ሲሞክሩ
አስተውለናል፡፡ በዚህም የትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤትና
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አጠቃላይ የሃይማኖት ነጻነትን
ጽንሰሀሳብና አንድምታ በሳቱ ምልከታዎች ትምህርትን
ከሀይማኖት ተጽዕኖ ነጻ መሆን አለበት /ሕገመንግስት አንቀጽ
90/ የሚለውን ድንጋጌ ከአውድ ውጭ በመተርጎም
በሀይማኖት ፍልስፍናዎች ውስጥ ጭምር እየገቡ ከጸሎትና
ከአለባበስ ጋር የተገናኙ ዝርዝር መመሪያዎችን በማውጣት
ጥሰቶችን ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡ ተጨማሪውና ዋናው ትችት
ጉዳዮቹ ከስልጣናቸው ውጭ መሆናቸውን መገንዘብ
አለመቻላቸው ነው፡፡
72 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !