Page 75 - አብን
P. 75

አብን


             አብን ብሄርና ሀይማኖት የሀገራችን የፖለቲካ ማደራጃ መርህ

             ሆነው  እንዳያገለግሉ  ለማድረግ  በሂደት  የተራዘመና  የተቀናጀ
             የመርህ  ማስረጽና  ተሞክሯዊ  ስምሪት  እንዲወሰድ  የበኩሉን
             አስተዋጽኦ  የሚያደርግ  ይሆናል፡፡  በተያያዘ  መልኩ  ባህልና
             ሀይማኖት  በሀገራችን  ውስጥ  የመገለጫዎች፤  የታሪካዊ
             እሴትና ትውፊቶች እንዲሁም እውቅና የማግኘትና የማጎልበት
             ስራዎች በነጻነት እንዲከናወኑ ህግና መርህ ተኮር አሰራሮችን
             እውን  ለማድረግ  የሚንቀሳቀስ  ይሆናል፡፡  የሀይማኖትና
             የማንነት  ብዝሀነት  የሀገራችን  አይነተኛ  መገለጫ  ሆነው

             እንዲቀጥሉ ለማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ እንዲዘረጋ በትጋት
             ይሰራል፡፡  በብዝሀነት  መካከል  ድንበር  ተሸጋሪ  የሆኑ  በጎ
             ቁርኝቶች  እንዲዳብሩና  ለሀገራዊ  አንድነት  የትስስር  መሰረት
             ሆነው  የህዝብ  ለህዝብ  ግንኑነትን  ለማጠናከር  አስቻይ
             ሁኔታዎችን ለመፍጠር በቁርጠኘነት ይሰራል፡፡


             1.2.   ሕገመንግስታዊ ማሻሻያ እንዴት?

              አብን  በመጭው  ምርጫ  በፌደራል  ደረጃ  የአብላጫ  ድምጽ
             ካገኘ የመጀመሪያው ተግባር የሚሆነው የሀሰት ትርክት አንግቦ
             ጨቋኝና  አግላይ  መዋቅር  እና  ስርዓት  የዘረጋውን  ሕገ
             መንግስት  እንዲለወጥ/እንዲሻሻል  ፖለቲካዊ  እርምጃ  መውሰድ
             ነው፡፡ አሁን ያለው ህገ መንግስት እንዳይሻሻል ተደርጎ በወቅቱ

             አሸናፊዎች  የተቆለፈበት  በመሆኑ  ህገ  መንግስቱን  ለማሻሻል
             ከአገዛዝ  ወደ  ዴሞክራሲያዊ  ስርዓት  ለመሸጋር  እንደሚፈልግ
             አገርየተለየ       ሂደት       ይጠይቃል፡፡አብን          በህገ     መንግስቱ
             ከተቀመጠው  የማሻሻያ  ሂደት  ውጭ  (Extra-constitutional
             amendment       procedure)      የሆነ     ፖለቲካዊ        መፍትሄ


               73   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   70   71   72   73   74   75   76   77   78   79   80