Page 80 - አብን
P. 80

አብን


          የሀብት  ክፍፍልን  የማረጋገጥ፣  በየዘርፉ  ጥራቱን  የጠበቀ

          አገልግሎትን  የማቅረብ  ኃላፊነታቸውን  በሚገባ  እንዲወጡ
          ያደርጋል፡፡

             1.6.   የመንግስትና የሃይማኖት የተለያዩ መሆን

             በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ሃይማኖቶች እና እምነቶች እኩል

             ህጋዊ  እውቅና  ይሰጣቸዋል፡፡  መንግስት  በሃይማኖት  ጉዳይ
             ጣልቃ  አይገባም፤  ሃይማኖቶችም  በመንግስት  ላይ  ጣልቃ
             አይገቡም፡፡  ይህ  እንደተጠበቀ  ሆኖ  የኃይማኖት  ተቋማት
             በአገራችን  ሰላም፣ልማት  እና  የአገር  በቀል  እውቀቶችን
             ለማስፋፋት የሚያደርጉትን አበርክቶ አብን ያበረታታል፡፡


             1.7.   የመሬት ባለቤትነት

             አብን  የከተማም  ሆነ  የገጠር  መሬትን  የሚያስተዳድር  ወጥ
             አገራዊ ፓሊሲ አለመኖሩ በአገራችን የመሬት ሃብት አስተዳደር
             ላይ  ያስከተለውን  ዘርፈ  ብዙ  ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ  ችግር
             ይገነዘባል፡፡ይህን  ችግር  ለመቅረፍ  ወጥ  አገራዊ  ፓሊሲ
             የሚያዘጋጅ  ሲሆን  የመሬት  ሃብትን  የሚያስተዳድር  ራሱን

             የቻለ ሚኒስትር መስሪያ ቤትም የሚያቋቁም ይሆናል፡፡ አሁን
             ያለው  የመሬት  ፖሊሲ  ያመጣውን  የፖለቲካ  እና  የኢኮኖሚ
             ምስቅልቅሎሽ  ለመቅረፍ  ይረዳ  ዘንድ  የመሬት  ባለቤትነትና
             ይዞታ      የግለሰብ፤የወል/የማህበረሰብና              የመንግስት        በሚል
             በሦስት  አይነት  የባለቤትነት/የይዞታ  ስርዓት  እንዲያዝ
             ይደረጋል፡፡





               78   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   75   76   77   78   79   80   81   82   83   84   85