Page 83 - አብን
P. 83
አብን
የሚቻለው የሚል እምነት አለው፡፡ ይህን ትልም እውን ሆኖ
ለማየት ደግሞ ለግል ዘርፍ እድገት ትኩረት የምንሰጠውን
ያህል የመንግሥት ዘርፍም በትክክለኛ አቅጣጫ መመራቱን
ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ በማምረት እና በአገልግሎት አቅርቦት
ሂደት የሃገሪቱን ሃብት በማሰማራቱ ረገድ የገበያው ስርዓት
ዋነኛውን ሚና እንዲጫወት መደረጉ መረጋገጥ አለበት፡፡
አዳዲስ የኢንዱስትሪ ግንባታዎች፣ የመረጃ ግኝትና እና
የቴክኖሎጂ ስርፀት፣ የከተሞች መስፋፋትና የግብርናውን
ዘርፈ ለማዘመን የሚደረጉ ጥራቶች ሳይዘነፉ፣ ጎን ለጎን
መራመዳቸውን ማረጋገጥ ዋነኛው የመንግስት የተቆጣጣሪነት
ሚናው ሊሆን እንደሚገባ እናምናለን፡፡
የኢኮኖሚ ልማት ዋነኛው እና ዓይነተኛው ግብ ድህነትን
በአጭር ጊዜ በመፍታት የመላ የሃገሪቱን ህዝብ የኑሮ ደረጃ
መሻሻል ሊሆን እንደሚገባ እንገነዘባለን፡፡ የመላውን ህዝብን
የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የህዝብን ስሜት ማዳመጥና ፍላጎቱ
በየጊዜው እየተሟላ መሄዱን ማረጋገጥ ዋነኛ ተግባራችን
ሊሆን ይገባል፡፡ በዚህ ሂደት የምርትና የአገልግሎት መጠን
እንዲጨምር ከሚሰጠው ትኩረት ባልተናነሰ መላው የሃገሪቱን
የተፈጥሮ ሃብት በቁጠባ ለመጠቀም እና የአካባቢ ምህዳሩን
ለመንከባከብ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ
ደግሞ ሁለገብ በሆነ መንገድ የሃገሪቱን መሬት፣
ተራራዎቻችን፣ ወንዞቻችንን፣ ጫካዎቻችንን፣ የእርሻ እና
የግጦሽ መሬቶቻችን፣ ሐይቆቻችን መጠበቅ እና መንከባከብ
ይኖርብናል፡፡ ለዚህም እንዲረዳን የምንከተለው የኢኮኖሚ
የእድገት ሞዴላችን/ትልማችን/ የአኗኗር ዘይቤያችንን ጭምር
81 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !