Page 81 - አብን
P. 81
አብን
የገጠርም ይሁን የከተማ የግል ይዞታ መሬት መሸጥ
መለወጥን ጨምሮ መሬቱን በማስያዝ ከባንክ መበደር፣
ለሦስተኛ አካል በውርስ ማተላለፍ ይቻላል፡፡አቅም ያላቸውና
ሰፋፊ መካናይዝድ እርሻዎችን ማልማት የሚፈልጉ
አርሶአደሮችም ሆነ ኢንቬስተሮች ቢፈልጉ ተከራይተው፣
ቢፈልጉ ከመሬት ባለቤቱ ጋር በሽርክና፣ሲፈልጉም ገዝተው
እንዲያለሙ በማድረግ ምግብ በማምረት ላይ የተሰማራውን
የአርሶ አደር ቁጥር እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡የመኖሪያ ቤት
ችግር ያለባቸው የአገራችን ህዝቦችም እንደአቅማቸው
በሚፈልጉበት አካባቢ ቦታ ገዝተው የመኖሪያ ቤት የመስራትና
የመኖር፣የቢዝነስ ተቋማትንና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን
የመገንባት መብት ይኖራቸዋል፡፡ ይህም ለመኖሪያ ቤት፣
ለከተሞችና ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ከፍተኛ ማነቆ የሆነውን
የቦታ አቅርቦትና ውድነት ይቀርፋል፡፡ በሌላ በኩል በመንግስት
ይዞታነት የሚገኙ መሬቶች ለአልሚዎች በሊዝ የሚተላፉበት
ስርዓት ይዘረጋል፡፡
1.8. የአዲስ አበባ ልዩ ሁኔታ
አዲስ አበባ የኢትየጵያ መንግስት እና የአፍሪካ ሕብረት ታሪካዊ
መዲና በመሆኗ እና በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ፣ በሕዝብ
ስብጥሯ፣ በምትጫወተው አገራዊና አለም አቀፋዊ ሚና
ምክንያት ከተማዋ የከተማ ራስ ገዝ ክልል (city state model)
እንድትሆን ይደረጋል፡፡ ከሌሎች የፌደራል ግዛቶች የሚስተካከል፣
የነዋሪውን ብዛት ከግምት ውስጥ ያስገባ፣ መንግስትና በፌደራል
ፓርላማ ተገቢው ውክልና እንዲኖራት በማድረግ የፌደራል
መንግስት መቀመጫ ሆና እንድትቀጥል ይደረጋል፡፡
79 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !