Page 84 - አብን
P. 84
አብን
ያገናዘበ፣ የአካባቢ ምህዳር በመንከባከብ የተቃኘ /Eco-
Friendly/ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
የኢኮኖሚ ልማት መርሃ-ግብራችን ለሳይንስ፣ ለቴክኖሎጅ፣
ለኢንጅነሪንግ እና ለሂሳብ ትምህርቶች ልዩ ትረት በሚሰጥ
ስርዓት ትምህርት ላይ መታነፁን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
በዚህ ዓይነት ስርዓተ - ትምህርት ያልተደገፈ የኢኮኖሚ
እድገት ትልም ውጤት ያለው የኢኮኖሚ ልማት ለማስገኘት
አይችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሃገራችንን የፋይናስ
ስርዓት፣ የገበያ ስርዓት፣ የአነስተኛ የኢኮኖሚ ተቋማት
የሚመሩበትን ዘዴና የማክሮ ኢኮኖሚውን የቁጥጥር ስርዓት
ማሻሻል /Reform/ ጎን ለጎን እንዲከናወኑ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡
የሃገራችንን የኢኮኖሚ ልማት እውን ሆኖ ለማየት ሃገሪቱ
መሰረት ልማት ማስፋፋትና ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡ ከሙስና
በፀዳ እና ግልፅነት በሰፈነበት መልኩ መንግስት በዚህ ዘርፍ
ዋነኛ የተዋናይነት ሚና ሊኖረው ይገባል፡፡ ይኸ ቁልፍ ዘርፍ
የሃገሪቱን የውሃ ማከማቻ ዴፖዎች፣ የባቡር ሃዲድ
መስመሮች ትላልቅ መንገዶች፣ የውሃ ትራንስፖርት፣
የአውሮፕላን ትራንስፖርት፣ ትላልቅ የነዳጅ እና የውሃ
ማስተላለፊያ ቱቦዎችን የሃይል ጣቢያዎችን፣ የመረጃና
የሎጅስቲክ መረቦችን ማስፋፋትና ማጠናከርን ይመለከታል፡፡
ይህን ዓይነት የዘመናዊ ኢኮኖሚ መሰረቶችን ለመገንባት እና
የተገነቡትም በተገቢ ሁኔታ አገልግሎች መሰጠታቸውን
ለማረጋገጥ የተማረ፣ በሙያ የሰለጠነ፣ የፈጠራችሎታው
የዳበረ ሰራተኛ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የፈጠራ
82 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !