Page 87 - አብን
P. 87

አብን


             በቀጥተኛ  የፋይናስ  ፍሰት  እንዲደገፍ  ጤነኛ  የሆነ  የተለያየ

             ደረጃ ያለው የካፒታል ገበያ እንዲኖር እንሠራለን፡፡ መንግስት
             የበጀት  ጉድለቱን  ለማካካስ  ሲል  አለአግባብ  በፖለቲካ  ውሳኔ
             ብቻ  በየጊዜው  ብር  እያተመ  የዋጋ  ንረቱ  የሚንርበት  ሁኔታ
             እንዳይኖር  ፣ይህ  ውሳኔ  የአሰራር  ነፃነቱ  ተጠብቆለት
             በሚደራጀው  የብሔራዊ  ባንክ  እንጂ  የመንግስት  አስፈፃሚ
             አካል ውሳኔ እንዳይሆን እናደርጋለን፡፡


             በሌላ  በኩል  ከፕራይቬታይዜሽን  ጋር  በተያያዘእስካሁን
             በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ተቋሞች ወደ
             ግሉ  ዘርፍ  የሚዛወሩበት  ሁኔታ  ከግሉ  ዘርፍ  ተዋንያኖች
             አቅምና  ጥንካሬ  ጋር  በተዛመደ  መልኩ  መሆን  አለበት፡፡  ወደ
             ግሉ  ዘርፍ  የሚዞሩበት  ሁኔታ  (Privatization)  የውጭ
             ኢንቨስተሮችን  በአካተተ  መልኩ  ሆኖ  መንግስት  የገጠመውን
             የፋይናስ ችግር ከመወጣት ጋር ሳይሆን፣ የቴክኖሎጅ ሽግግር

             የሚሳለጥበትን፣ ለተጠቃሚው ህዝብ የሚቀርበው አገልግሎት
             ጥራት ያለውና በአነስተኛ ዋጋ የሚቀርብበትን ሁኔታ ባገናዘበ
             መልኩ እንዲከናወን ይደረጋል፡፡

                  የመንግሥት  የኢኮኖሚ  ነክ  ዓላማዎች  እና  ተቋማዊ
                  ይዞታ
             በማናቸውም  ዘመናዊ  ኢኮኖሚ  መንግሥት  የተወሰነ  ተግባር

             እንዲኖረው  መደረጉ  የማይታለፍ  ሲሆን  ከፍተኛ  ጥራት
             ያላቸው  ተቋማት  በመንግስታዊ  የኢኮኖሚ  ዘርፍ  መኖራቸው
             የግድ

             በኢኮኖሚው ውስጥ መንግስት የሚጫወታቸው ሚናዎች



               85   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   82   83   84   85   86   87   88   89   90   91   92