Page 92 - አብን
P. 92
አብን
በመሆኑም አብን በምርጫ አሸንፎ መንግስተ ቢሆን በሃገሪቱ
ዘላቂነት ያለው ልማትና የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር
የሚከተሉትን ማስተካካያዎች ያደርጋል፡፡
2.2.1.ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ
ሀ. የገንዘብ/ሞኒታሪ ፓሊሲ
የማንኛውም ሃገር ሞነታሪ ፓሊሲ ተቀዳሚ ተግባር የመሆነው
ጥብቅ የሆነ የገንዘብ አቅርቦት (money supply) ቁጥጥር
በማድረግ የተረጋጋ የዋጋ ግሽበት በሃገሪቱ ውስጥ እንዲኖር
ማስቻል ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የሃገራችን ሞኒታሪ ፓሊሲ
ለዘመናት ከፍተኛ ድከመት የነበረበት ነው፡፡ አመታዊ የዋጋ
ግሽበት በለሁለት አሃዝ መሆን ከጀመረ ከአስር አመታት በላይ
ሆነው፡፡ ይህም ቋሚ ገቢ ያላቸውን የመንግስትና የግል
ተቋማት ተቀጣሪ ሰራተኞች ብሎም በአንፃራነት ከንግድ ስራ
ውጭ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሆኔታ እጅግ ፈታኝ
ሁኔታ ውሥጥ ከቶታል፡፡ሞኒታሪ ፓሊሲ የወለድ ምጣኔን
መሰረት በማድረግ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚኖረውን የብድር
አቅርቦት ይወስናል፡፡ ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ የብድር
አቅርቦትን በማስፋት ኢንቨስትመንትን ያበረታታል፡፡ በዚህም
የኢኮኖሚ እድገትን ያማጣል፡፡ ስለዚህም አብን በበብሔራዊ
ባንክ በኩል የገንዘብ አቅረቦትንናየወለድ ምጣኔን መስረት
ያደረገ የሞኒታሪና ፓሊሲና የአሰራር ማሻሻያ (በዋናነት የዋጋ
ግሽበትን ለመቆጣር ያለመ) ይደረጋል፡፡ አላማውንም በተሳካ
ሁኔታ ይፈፅም ዘንድ ስልጣን ከያዘው መንግስት ገለልተኛና
ነፃ የሆነ አደረጃጀት እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ብሄራዊ ባንክ
ለንግድ ባንኮች ለአጭር ጊዜ የሚያበደርበት ምጣኔ (Discount
90 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !