Page 93 - አብን
P. 93
አብን
Rate)፣ ንግድ ባንኮች ከአጠቃላይ ተቀማጫቸው በብሔራዊ
ባንክ ተቀማጭ የሚያደርጉት ምጣኔ (Reserve equirments)፣
የግምጃ ቤትና ሌሎች ሰነዶችን የሚገዛበትና የሚሸጡበትን
አሰራር (Open market operations) የሚኒተሪ ፓሊሲ አላማውን
መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲሰሩ በሰው ኃይልና ቴክኖሎጅ
አጠቃቀም ከፍተኛ የሆነ የአቅም ግንባታ ይሰራል፡፡
ለ. የበጀት/ፊስካል ፓሊሲ
የበጀት ፓሊሲ (Fiscal policy) በግብርና በመንግስት የወጭ
በጀት ፓሊሲዎች እድገት እንዲመጣ ያደርጋል፡፡ በማክሮ
ኢኮኖሚ ደረጃ የኢኮኖሚ መረጋጋትን እና የስራ እድልን
በመፍጠር፣ኢንቨስትመንትን እና ምርታማነትን በማሳደግ
ወሳኝ ሚናን ይጫወታል፡፡ በእቅድና በጥንቃቄ የተመራ የታክስ
ማበረታቻ የግል ኢንቨስትመንትን ለማነቃቃት ውጤታማ
መንግሰታዊ ኢንቨስትመንት በመሰረተ ልማቶች እንዲኖር
ይረዳል ፡፡
በረጅምና መካከለኛ ጊዜ የኢኮኖሚ እድገት ላይም ከፍ ያለ
ተፅኖ ያሳድራል፡፡ የመንግሰት ወጭዎች በመሰረተ ልማት
(መንገድ፣ ወደብ፣ ቴሌኮም፣ የሃይል ማመንጫ በአምራች
ደርጅቶች እና ኢንዱሰተሪዎች ላይ ምርታማነትን በማሳደግ
ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ በተመሳሳይ በትምህርት እና ጤና
ላይ መንግስት የሚያደርገው ኢንቨስትመንት የሰው ሃይልን
አቅምና ምርታማነት በማሳደግ በረዥም ጊዜ ቀጣይነት ላለው
ዕደገት ወሳኝነት አለው፡፡ በአጭሩ ፊስካል ፓሊሲ
የሚከተሉት አላማዎች ይኖሩታል፡-
91 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !