Page 96 - አብን
P. 96
አብን
«በየነ ግብር» የተሰኘ በቴክኖሎጂ የታገዘ
የግብር አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት
በአገራችን በአሁኑ ሰዓት ግብር ለመክፈል በራሱ ከባድ ሰራ
የሆነበት አሰራር ላይ እንገኛለን፡፡ ግብር ከፋዩ ለግብር
አስተዳደሩ የሚወስደው ግዜና ወጭ ከመደበኛው የንግድ
ስርዓት በላይ የሚጨነቅበት ነው፡፡ ይህን ቀላል ለማድረግ
ከግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ጀምሮ ክፍያ መፈፀም፣ ማሳወቅ፣
ክሊራንስ መውሰድ ድረሰ ግብር ከፋዩ የታክስ መ/ቤቱ በአካል
ቀርቦ መጉላላት ሳይጠበቅበት በቀላሉ በቴክኖሎጂ በመጠቀም
የሚፈፅምበት አሰራር ይዘረጋል፡፡
ግምታዊ ግብር አጣጣልና አወሳስን እናስቀራለን
ግምት እንደ በግለሰቦች ግምት እና ይሁንታ ላይ የተመሰረተ
ነው፡፡ ብዙ ግብር ከፋዮቸና ከንግድ ያስወጣ፣ ቀያቸውን ለቀው
እንዲሄድ ያደረገ፣ ጥሪት ሃብታቸውን ያሸጠ አሰራር በመሆኑ
ይህን አሰራር እናስቀራለን፡፡ ትንንሽ የንግድ ተቋማት
በራሳቸው ፈቃድ እንዲያሳውቁ ማድረግ ፣ መካከለኛ እና
ትልልቅ ግብር ከፋዮች በሽያጭ መመዝገቢያ ቴክኖሎጂ
መሣሪያ እንዲጠቀሙ ይደረጋል፡፡ ይህ አሰራር ተዘርግቶ
ግብር ስወራ ላይ በሚሳተፉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ
ጥናቶችን መሰረት ያደረገ የህግ ማስከበር ስራ ይሰራል፡፡
የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያን በነፃ ለግብር
ከፋዩ ማቅረብ
በፈቃዳኝነት የሚከፈልን ግብር ለማበረታት ግብር ከፋዮች
የግብር እንቅስቃሴውን በቴክኖሎጂ እንዲመዘገብ ከማስገደድ
94 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !